Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የቤተሰብ ጸሎት ሰዓት

    የጥዋትና የማታ ጸሎት መሪ ስለሆነ አባትዮው የቤተሰቡ ካህን ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ባለቤቲቱና ልጆቹ በጸሎትና በመዝሙር ሊተባበሩት ይገባል፡፡ ጥዋት ወደ ሥራ ከመሔዱ በፊት አባትዮው ልጆቹን ሰብስቦ በጸሎት ለሰማይ አባታቸው አደራ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የቀኑ ተግባር ከተከናወነ በኋላ ቤተሰቡ በአንድ ላይ ተሰብስበው ቀኑም በደህና ላዋላቸው አምላክ በጸሎና በመዝሙር ምስጋና ያቅርቡ፡፡CLAmh 35.1

    አባትና እናት የሆኑ ሁሉ ምንም እንኳ ሥራቸው ከባድ ቢሆን ከልጆቻቸው ጋር ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብን መርሳት አይገባቸውም፡፡ በትዳርችሁ መላዕክት እንዲመርዋችሁ ለምኑ፡፡ የምትወዷቸው ልጆቻችሁ ፈተና እንደሚያጋጥማቸው አትርሱ፡፡ የየቀኑ ብስጭት ሽማግሌና ወጣትን ያሰናክላል፡፡ የፍቅር፤ የትዕግስትና የደስታ ሕይወት ለመኖር የሚመኙ ሁሉ መጸለይ አለባቸው፡፡ ራሳችንን ለማሸነፍ የምንችለው ከእግዚአብሔር የማያቋርጥ ርዳታ ስናገኝ ብቻ ነው፡፡CLAmh 35.2

    ቤተሰብ ማለት ደስታ፣ መከባበርና ፍቅር የሚገኝበት ቦታ ነው፡፡ እነዚህ ጥሩ ጠባዮች በሚገኙበት ቦታ ደስታና ሰላም ይሰፍናሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ችግር ያጋጥም ይሆናል፤ ይህ የሰብአዊ ፍጡር ዕድል ነው፡፡ ቀኑ የጨገገ ቢመስል ትዕግሥት፣ ምስጋና ፍቅር እንደ ፀሐይ በልብ ውስጥ ያብሩ፡፡ እነዚህ ጠባዮች ባሉበት ቦታ የእግዚብሔር መላዕክት ይገኛሉ፡፡CLAmh 35.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents