Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    18—የጤና ጎዳና

    ሕይወታችንን ለመጠበቅ፤ ሊጠግነንና ሊያድነን እግዚአብሔር በተፈጥሮ አማካይነት ከቀን ወደቀን፤ ከሰዓት ወደ ሰዓት፤ ከቅጽበት ወደ ቅጽበት ይሠራል፡፡ ከአካል ክፍላችን አንዱ ጉዳት ሲደርስበት የጥገናው ተግባር ወዲያውኑ ይቀጥላል፡፡ የተፈጥሮ መሣሪያዎች ለሥራ ታጥቀው ይሰለፋሉ፡፡ ግን በእነዚህ መሣሪያዎች አማካይነት የሚሠራው የእግዚአብሔር ሐይል ነው፡፡ የሕይወት ምንጭ እርሱ ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰው ከበሽታ ሲያገግም የፈወሰው እግዚአብሔር ነው፡፡CLAmh 95.1

    በሽታ፣ ሥቃይ፣ ሞት የክፉ ኃይል ተግባሮች ናቸው፡፤ ሰይጣን አጥፊ፤ እግዚአብሔር ግን ሠሪ ነው፡፡ ለእሥራኤል የተነገሩት ቃላት ዛሬም የአካል፣ የመንፈስና የአእምሮ ፈውስ የሚያገኙትን ሰዎች ሁሉ ይጠቅሳሉ፡፡ “እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ፡፡” (ዘጸዓት 15፡16)CLAmh 95.2

    “ወዳጄ ሆይ፤ ነፍስህ እንደሚከናወንልህ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ፡፡” የሚለው አነጋገር እግዚአብሔር ለሰብዓዊ ፍጡር በሙሉ ያለውን በጎ ፈቃድ ይገልጣል፡፡ (3ኛ ዮሐንስ 2)CLAmh 95.3

    “ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፤ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፤ ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድን፤ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፤ ምኞትሽን በበረከት የሚያጠግባት” እግዚአብሔር ነው፡፡ (መዝሙር 103፡3፣4)CLAmh 95.4

    ክርስቶስ ሰዎችን ከኃጢአታቸው ሲፈውስ ብዙዎቹን “ከዚህ የከፋ እንዳያገኝህ ደግመህ አትበድል” ይላቸው ነበር፡፡ (ዮሐንስ 5፡14) ፡፡ በዚህ አባባሉ ሰዎች በራሳቸው ላይ በሽታን የሚያመጡ የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላፍ መሆኑንና ጤናቸው ሊመለስላቸው የሚችልም ሕጉን በመጠበቅና በመታዘዝ ብቻ መሆኑን አስተማረ፡፡CLAmh 95.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents