Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከማስታገሻ መድኃኒቶች ተጠንቀቁ

    ጤናን ከሚያጓድሉትና ሕመምን ከሚያባብሱት ነገሮች ሁሉ ተቀዳሚነት ያለው መርዘኛ መድኃኒቶችን እንዳገኙ መውሰድ ነው፡፡ ሲታመሙ የበሽታውን ጠንቅ ለማወቅ የሚጥሩ ጥቂቶች ናቸው፡፤ ፍላጎታቸው ለጊዜው የሚሰማቸውን ሥቃይና ችግር ማስታገስ ነው፡፡ ስለዚህ ጥቅምና ጉዳታቸውን ለይተው የማያውቋቸውን ማስታገሻ መድኃኒቶች ከኪወስክ ገዝተው ይቅማሉ፡፡ ወይም ለጤና ተጻራሪ ከሆነው የኑሮ ልምዳቸው ሳይታቀቡ ሐኪሙን እንዲያክማቸው ይጠይቁታል፡፡ የተቀመሰው መድኃኒት ካልፈወሰ ሌላ መድኃኒት ይደገምበታል፤ ያም ካላሻለ ሦስተኛ መድኃኒት ይሠለስበታል፡፡ በሽታው እየተባባሰ ይሄዳል፡፡CLAmh 98.2

    ሕመም የጤና ሕግ ሳይከበር ሲቀር የሚፈጠረውን መቃወስ የአካል ክፍሎች ለማስተካከል ሲሞክሩ የሚፈጠር ሁኔታ ነው፡፡CLAmh 98.3

    በሽታ የዞረው ሰው ጠንቁን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፤ ለጤና የማይስማማ ይዞታ፣ የተሳሳተ ልማድ ሊታረም ይገባል፡፡ ተፈጥሮ ቆሻሻውን አጣርታ በአካል ውስጥ የተስተካከለ አቋም ለመመሥረት በምታደርገው ጥረት ርዳታ አይነፈጋት፡፡CLAmh 98.4

    እንዳገኙ ማግበስበስ ትርፉ በሽታ ነው፡፡ ተፈጥሮ የምትፈልገው ከአላግባብ ከሚጫንባት ሸክም ነፃ መውጣትን ነው፡፡ ሥራ የበዛበት የምግብ ማዋረጃው ክፍል ዕረፍት እንዲያገኝ በሽተኛው ሁለት ወይም ሶስት ምግብ ጊዜያት ቢጾም በጣም ጥሩ ነው፡፡ የአእምሮ ሥራ ብቻ ለሚሰሩ ሰዎች ለአንድ ሰሞን ፍራፍሬ ብቻ ሲመገቡ ብዙ ጊዜ ትልቅ መሻሻል ይታይባቸዋል፡፡ ለብዙ ጊዜ ከጾሙ በኋላ መጠነኛ ምግብ መብላት ለጤና ተስማሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡CLAmh 99.1

    ለሁለት ወይም ለሦስት ወራት የተወሰነ ምግብ ቢመገቡ በሽተኞች የጤና ምንጩ ራስን መቆጣጠር መሆኑን ባወቁ ነበር፡፡CLAmh 99.2

    አንዳንዶች ሥራ በማብዛት ራሳቸውን ከበሽታ ላይ ይጥላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከመጨነቅ ነፃ ቢሆኑና ቢያርፉ ምግባቸውን ቢቆጣጠሩ ይሻላቸዋል፡፡CLAmh 99.3

    አእምሮአቸው የታወከባቸውና በተጨናነቀ አካባቢ የሚኖሩ ከሰቀቀን ነጻ ሆነው ተዝናንተው ሊኖሩ ወደሚችሉበት ወደ ገጠር ለዕረፍት ቢሄዱና ተፈጥሮን ቢመለከቱ ጤናቸው ይመለስላዋል፡፡ እርሻና ጫካዎችን እየዞሩ መመልከት፤ አበባዎችን መቅጠፍ፣ የወፎችን ጩኸት መስማት፣ ማንኛውም መድኃኒት ከሚሰጠው ፈውስ የበለጠ መሻል ያስገኛል፡፡CLAmh 99.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents