Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሚያኮራ ጀግንነት

    የዮሴፍንና የዳንኤልን ታሪክ አስታውሱ፡፡ እግዚአብሔር ሊጎዷቸዉ ያሰቡትን ሰዎች ሤራ አላስቀረም፡፡ ግን በመከራና በጭንቀት ጊዜ ጽኑ እምነት ላሳዩት ወዳጆች የታቀደባቸውን ተንኮል ወደ በጎ ነገር ለውጠላቸው፡፡CLAmh 202.1

    በዓለም እስካለን ድረስ ልዩ ልዩ ነገር ያጋጥመናል፡፡ ጠባያችን የሚያስገምቱ የሚያስቆጡ ነገሮች ይደርሱብናል፡፡ የክርስቲያናት እድገት የሚጎለምሰው ክፉን በበጎ ለማሸነፍ በመሞከር ነው፡፡CLAmh 202.2

    ክርስቶስ በውስጣችን ካለ ቅር የሚያሰኝ ነገር ቢደርስብን እንኳ ትዕግስተኞች፤ ደጎች፤ የማንሰለችና ደስተኞች ልንሆን እንችላለን፡፡CLAmh 202.3

    ከቀን ወደ ቀን ከዓመት ወደ ዓመት ራሳችንን በማሸነፍ የሚያኮራ ጀግንነት እናገኛለን፡፡ ዋና ተግባራችን ይህ ነው፡፡ ግን ይህ ታላቅ ተግባር የክርስቶስ ርዳታ ካልተጨመረበት፤ ቁርጥ አሳብ ካላደረግን፤ የማያወላውል አስተሳሰብ ከሌለን፤ የዘወትር ትጋት ካላሳየን፤ በጸሎትም ካልተጋን ከግብ ሊደርስ አይችልም፡፡ እያንዳንዱ ግለ-ሰብ የየራሱ ጦር ሜዳ አለበት፡፡ ከእርሱ ጋር ካልተባበርን በቀር እግዚአብሔር ራሱ እንኳ ጠባያችንን ጨዋ፤ ኑሮአችንን ጠቃሚ ሊያደርገው አይቻልም፡፡ ከጦርነቱ የሚያፈገፍግ ሁሉ አቅም ያንሳቸውና ከድልነሺነት የሚገኘው ደስታ ይቀርባቸዋል፡፡CLAmh 202.4

    የደረሰብንን ችግር፤ ኀዘናችንና ትካዜአችንን መዝግበን መያዝ አያሻንም፡፡ ሁሉ ነገር በሰማይ መጽሐፍ ስለተመዘገበ የሰማይ አምላክ መፍትሔ ይሻለታል፡፡CLAmh 202.5

    መጥፎ መጥፎውን ነገር ብቻ ስናስታውስ በየጊዜው የማይለየንን የእግዚአብሔርን ምህረት ፥ መላዕክትን የሚያስደንቀውን እግዚአብሔር ልጁን በመስጠት የገለጠልንን ፍቅሩን የመሳሰሉትን በረከቶች እንረሳቸዋለን፡፡CLAmh 202.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents