Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የፈቃድ ኃይል

    የፈቃድ ኃይል የተፈለገውን ያህል ግምት አልተሰጠውም፡፡ ፈቃዳችን በንቃት ትክክለኛውን አቅጣጫ ይያዝ እንዲህ ከሆነ ለሰውነታችን በሙሉ የኃይል ምንጭ ይሆናል፤ ጤና ለማሟላት ጠቃሚ ርዳትን ያስገኛል፡፡ በሕመም ጊዜም ብርቱ ፈቃድ ወይም ቆራጥነት ካለ መቋቋም ይቻላል፡፡CLAmh 109.1

    በሚገባው አቅጣጫ ከተመራ አሳብን ይቆጣጠራል፡፤ የአካልንና የአእምሮን በሽታዎች ለመቋቋም ለማሸነፍ ዋና መሣሪያ ይሆናል፡፡ በቆራጥነት ኃይል አማካይነት በኑሮ ትግል ውስጥ ተካፋይ በመሆን ሐኪሙ ሊያድናቸው በሚያደርገው ጥረት ተባባሪ መሆን ይችላሉ፡፡ ከቆረጡ ሊድኑ የሚችሉ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ፡፡ እግዚአብሔር በሽተኞች እንዲሆኑ አይፈልግም፡፡ ጤነኞና ደስ ያላቸው እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ እነርሱም በበኩላቸው ጤናማ እንዲሆኑ በጥብቅ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ በሽተኞች ለሕመም አልጠቃም በሚል ጠንካራ መንፈስ ከተነሳሱና እንዲሁ አካላቸውን አስንፈው ካልተቀመጡ ሊድኑ ይችላሉ፡፡CLAmh 109.2

    ሥቃይና ሕመም ቢሰማቸውም ለአቅማቸው ተስማሚ የሆነ ጠቃሚ ሥራ መሥራት ይሞክሩ፡፡ ቀላል ሥራ ሲሠሩ የፀሐይ ሙቀትና ንጹህ አየር እንደልባቸው ስለሚያገኙ ብዙ በሕመም የተሰነከሉ ድውያን ጤናማዎችና ብርቱዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡CLAmh 109.3

    ጤናቸውን መመለስና መጠበቅ ለሚያሻቸው እንዲህ የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አለ፡፡ “መንፈስ ይሙላላችሁ እንጅ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይህ ማባከን ነውና፡፡” (ኤፌሶን 5፡18)CLAmh 109.4

    እውነተኛ ፈውስና የአእምሮ ብርታት የሚገኘው በማይገባ ምግብና መጠጥ አማካይነት አይደለም፡፡ ያለ እግዚአብሔርና ያለ ተስፋ የሆኑ በሽተኞች አሉ፡፡ በመጥፎ ምኞት፤ በአሰቃቂ ተግባር በሕሊና ወቀሳ ይሰቃያሉ፤ ከዚህ ዓለም ሕይወት ሊሰናበቱ ነው፤ ለሚመጣው ዓለምም ተስፋ የላቸውም፡፡ አስታማሚዎቹ ለእነዚህ ሰዎች ያልሆነ ነገር በመፍቀድ ሊያስደስቷቸው አይሞክሩ፡፡ የኑሮአቸው ነቀርሳ የሆኑት እነዚያ ያልተገቡ ልምዶች ናቸው፡፡ የተራበና የተጠማ ነፍስ አጥጋቢ ነገር ካላገኘ አይረካም፡፡ ራስን በመውደድ በደስታና በተድላ መንፈላሰስ ራስን ማታለል ነው፡፡ አንዳንዶች አጉል ስሜትን ከብርታት ለይቶ ማወቅ ይሳናቸዋል፡፡ ጊዜያዊ ስሜታቸው ሊያልፍ ደስታቸው ያበቃል፡፡ ከዚያ በኋላ ኀዘንና ሰቀቀን ይጫጫናቸዋል፡፡CLAmh 109.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents