Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እውነተኛው የብርሃን ምንጭ

    ብዙ ሰዎች ትምህርት ለማግኘት በመናፍቃን የተጻፉትን መጻሕፍት ማንበብ ግዴታ ነው ይላሉ፤ ይህንም የሚሉበት ምክንያት በመጽሐፎቻቸው ጥሩ ጥሩ አሳቦች ስለሚገኙ ነው፡፡ ነገር ግን የነዚህ አሳቦች ጠንሳሽ ማነው? እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ የብርሃን ሁሉ ምንጭ እርሱ ነው፡፡ እውነትን በቀላሉ ለማግኘት ስንችል ገና አንዳንድ አሳቦች እናግኝ ብለን ከስሕተት ረግረግ ውስጥ ገብተን የምንዛግጠው ለምንድን ነው?CLAmh 43.4

    ከእግዚአብሔር መንግስት ጋር በመዋጋት ላይ ያሉ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ያለ ጥበብ የሚኖራቸው ለምን ይሆን? ሰይጣን የተማረው በሰማይ አደባባይ ነው፡፡ የክፉና የደግም እውቀት አለው፡፡ የከበረውን ነገር ከረከሰው ጋር ያቀላቅለዋል፡፡ ለማታለል የሚያስችው ይህ ነው፡፡ ሰይጣን የሰማያዊውን ብርሃን ልብሱን አውልቆ ስለጣለ የብርሃን መልአክ ልንለው እንችላለን ወይ? ፈታኙ በእርሱ እቅድ የሰለጠኑ፤ በእርሱ መንፈስ የተነቃቄና የሥራው ልምድ ያላቸው ወኪሎች አሉት፡፡ ከእነርሱ ጋር እንተባበር ወይ? የወኪሎቹን ሥራስ ለትምህርት አስፈላጊ ነው ብለን እንቀበል ወይ?CLAmh 43.5

    የመናፍቃንን ትምህርት ለመከተል የሚጠፋው ጊዜና ጉልበት የከበረውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማስተማር ብንጠቀምበት በጨለማና በሞት ጥላ ሥር የሚኖሩ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በሕይወት ብርሃን በተደሰቱ ነበር፡፡CLAmh 44.1

    ቤተመጻሐፍት በታሪክና በሃይማኖት ማስተማሪያ ትልልቅ መጻሕፍት ተሞልተው ሳለ ምግብ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ገንዘብ እናባክናለን ብዬ አስባለሁ፡፡ በነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ልናገኘው ከምንችለው የበለጠ ከዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ልናገኝ እንችላለን፡፡ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም፤” ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡” በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡” “እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው፡፡” ዮሐ 6፡35፣51፣47፣63CLAmh 44.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents