Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በታላቁ ሐኪም ማመን

    በማሰብ ምክንያት የመጣውን በሽታ ለማከም ታላቅ ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ የቈሰለ ልብ፣ ተስፋ የቆረጠ አእምሮ የደግነት ሕክምና ያስፈልገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ መፍትሄ ያጣ የቤት ጣጣ እንደ ነቀዝ ኑሮን ያደቃል፡፡CLAmh 108.2

    አንዳንድ ጊዜም ኃጢአት የአእምሮን ሚዛን ያቃውስና ጤና ይነሣል፡፡ የዚህ ዓይነት ድውያን ሊረዱ የሚችሉ በፍቅርና በመተዛዘን ነው፡፡CLAmh 108.3

    ሐኪሙ መጀመሪያ እንዲተማመኑበት ካደረገ በኋላ ወደ ታላቁ ሐኪም ያመልክታቸው፡፡ በእውነተኛው ሐኪም ካመኑ፤ በነገሩ እንደሚያስብበትም ከገባቸው አእምሮአቸው ሰላም ያገኛል፤ ጤናቸው ይመለሳል፡፡CLAmh 108.4

    ፈገግታ በማይታይበት ፊት የተራራቀ ሕክምና ከማድረግ ይልቅ በርህራሄና በዘዴ የተደረገ ሕክምና የበለጠ ውጤት ይሰጣል፡፤CLAmh 108.5

    ብዙዎች ዕውነቱን ብንናገር በሽተኛው ይደነግጣል ብለው በመስጋት ትድናለህ የሚል የውሸት ተስፋ ይሰጡታል፡፡ እንዲያውም በሽተኛው የበሽታውን አደገኛነት ሳያውቅ ከመሞት ይደርሳል፡፡ ይህ አድራጎት ቂልነት ነው፡፡ ለበሽተኛ የሕመምን አደገኛነት መግለጡ የተሻለ ዘዴ ላይሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ነገሩ ተስፋ ያስቆርጠውና እንዳይድን ያደርገዋል፡፡ በሽታቸው የፍርሃት ለሆነ ሰዎች እውነቱን በሙሉ መዘርዘር አያሻም፡፡ የዚህ ዓይነት ሰዎች ብዙዎቹ የማያመዛዝኑ ስለሆኑ ራሳቸውን የመቈጣጠር ልምድ የላቸውም፡፡ የተለዩ ነገሮች ስለሚያስደስቷቸው ስለራሳቸውና ስለሌሎች ተሳሳተ አስተሳሰብ አላቸው፡፡ ስህተቱ ትክክል መስሎ ይታያቸዋልና ለእነርሱ የሚጠነቀቁ ሰዎች በትዕግሥት ሳይሰለቹ ተግተው መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡ ለእንደነዚህ ያሉት ሰዎች ስለራሳቸው በግልጥ ሳይደበቅ ቢነገራቸው አንዳንዶቹ ቅር ሲሰኙ ሌሎቹ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡CLAmh 108.6

    የሱስ ለደቀመዛሙርቱ “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም” አላቸው፡፡ (ዮሐንስ 16፡12) ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እውነቱን መደበቅ ቢያስፈልግም ማታለል በምንም ሁኔታ አስፈላጊና የሚደገፍ አይደለም፡፡CLAmh 108.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents