Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    “ራስህን እወቅ”

    እያንደንዱ ሕፃንና ወጣት ራሱን ማወቅ አለበት፡፡ እግዚአብሔር የሰጠውን ሥጋዊ አካሉን ሊያስተውልና ጤነኛ እንዲሆን የሚያደርጉትንም ሕጎች ማወቅ ይገባዋል፡፡ ሁሉም ዋና ዋናዎቹን የትምህርት ቅርንጫፎች ማወቅ ይገባቸዋል፡፡ ለየቀኑ ሕይወት ገጣሚ የማያደርጋቸው የተግባረ ዕድ ትምህርት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በዚህ እውቀት ላይ የወንጌል ሥራ የማስፋፋት ልምድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡CLAmh 41.1

    ወጣቶች የቻሉትን ያህል በተቻላቸው ፍጥነት ዕውቀትን ለማግኘት ይገስግሱ፡፡ ችሎታቸው የፈቀደላቸውን ያህል ዕውቀታቸው ሰፊ ይሁን፡፡ በሚማሩበት ጊዜ ዕውቀታቸውን ያካፍሉ፡፡ በዚህ አኳኋን አእምሯቸው ኃይልና መሠረት ያገኛል፡፡ የትምህርታቸው ጥቅም የሚታወቀው ሲሠሩበት ነው፡፡ ያወቁትን ሳያካፍሉ በትምህርት ላይ ብዙ ጊዜ ማሳለፍ ብዙውን ጊዜ ለእውነተኛ ዕድገት ረዳት ከመሆን ፈንታ እንቅፋት ይሆናል፡፡ በቤትም ሆነ በትምህርት ቤት ተማሪው እንዴት እንደሚያጠናና የሚያውቀውንም እንዴት ማካፈል እንደሚገባው መማር አለበት፡፡ የሕይወቱ ሥራ ምንም ዓይነት ቢሆን በሕይወቱ ሙሉ ተማሪና አስተማሪ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔርን መታመኛው አድርጎ፤ ለሚያምኑት ማንኛውንም ጥያቄ ሊመልስ ከሚችለውና ጥበቡ ከ-እስከ ከሌለው አምላክ ጋር በመጠጋትና በእርሱ በመታመን ዘወትር ሊያድግ ይችላል፡፡CLAmh 41.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents