Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አስደሳች ጠባይ ይኑርህ

    እናቲቱ አስደሳችና በቃኝ ማለት ያለባት ጠባይ እንዲኖራት ለማድረግ ትማር፡፡ ይህን ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ዋጋ የልጆችዋ የአካልና የሞራል ደኅንነት ነው፡፡ ተደሳች መንፈስዋ ለቤተሰብዋ ደስታን ያመጣል፡፡ በበለጠም የራስዋን ጤና ያሻሽለዋል፡፡CLAmh 24.2

    ባልዮው በርኅራኄና በተሟላ ፍቅር ባለቤቱን ሊዳር ይገባል፡፡ በቤትዋ እንደ ፀሐይ የምታበራ ያልሰለቻትና ተደሳች እንድትሆን ከፈለገ ከሸክምዋ ይርዳት፡፡ ደግነቱና የፍቅር አክብሮቱ ያደፋፍራታል፤ የሚሰጣትም ደስታ ለራሱ ደስታና ሰላም ያመጣለታል፡፡CLAmh 24.3

    የጨገገው፣ ራሱን ብቻ ወዳጅና ጨቋኝ የሆነ ባል ለራሱ ደስታ የሌለው ከመሆኑም በላይ በቤቱ ውስጥ የሚገኙትንም ሁሉ ደስታ የሌላቸው ያደርጋቸዋል፡፡ ለዚህም የሚያገኘው ዋጋ የሚስቱ ተስፋ መቁረጥ፣ ጤና ማጣትና ፍቅር በሌለው ተቆጭነቱ ምክንያት የልጆቹ መበላሸት ነው፡፡CLAmh 24.4

    እናቲቱ የሚገባትን ጥቃቄና ምቾት የተነፈገች እንደሆነና ያለ መጠና በመሥራት ወይም በኀዘንና በትካዜ ኃይልዋን የጨረሰች እንደሆነ ልጆችዋ ሊወርሱት የሚገባቸውን የአእምሮ ኃይልና ተደሳችነት አያገኙም፡፡ የተሻለው ግን የልጆቹን እናት ማስደሰት፣ እንዳትቸገር ማድረግ፣ ጉልበትዋን የሚጨርስ ሥራ አለማሠራት ከሰቀቀን ሁሉ ማዳንና ልጆቹም የሕይወትን ጣጣ በገዛ ራሳቸው ለማሸነፍ የሚያስችላቸውን ኃይል እንዲወርሱ ማድረግ ነው፡፡CLAmh 24.5

    ለልጆቻቸው የእግዚአብሔር ወኪል ስለሆኑ የወላጆች ኃላፊነት በጣም ከባድ ነው፡፡ በጠባያቸው፣ በየዕለት ኑሯቸውና በማስተማር እቅዳቸው የእግዚአብሔር ቃል ለልጆቻቸው ይተረጐማል፡፡ የእነሱ ሁናቴ ልጆቻቸው የእግዚአብሔርን እርግጠኛ ተስፋ እንዲቀበሉ ወይም እንዲንቁ ያደርጋቸዋል፡፡CLAmh 24.6

    እግዚአብሔር እንደሚፈልግባቸው በመኖራቸው ምክንያት ልጆቻቸው የእግዚአብሄርን ሕግ እዲወዱና እንዲያከብሩ፤ በደግነታቸው፣ በቅንነታቸውና በትዕግስታቸው ምክንያት ለልጆቻቸው የእግዚአብሔርን ጽድቅና ትዕግስት የሚያስረዱ፤ እንደዚሁም ልጆቻቸው እንዲወዷቸው፣ እንዲያምኗቸውና እንዲታዘዟቸው በማድረጋቸው ምክንያት እግዚአብሔርን እንዲወዱ፣ እንዲያምኑና እንዲታዘዙ የሚያደርጉ ወላጆች የተባረኩ ናቸው፡፡ እንደዚህ ያለ ስጦታ ለልጆቻቸው የሚሰጡ ወላጆች ሁሉ ከሁሉ የበለጠ ዘላለማዊ ሐብት አወረሱ ማለት ነው፡፡CLAmh 24.7

    እንድትጠነቀቅላቸው ልጆች በመሰጠትዋ እያንዳንዷ እናት ከእግዚአብሔር ትልቅ አደራ ተሰጥቷታል፡፡ “ይህን ልጅ ወይም ይህችን ልጅ ወስደሽ አስተምሪልኝ፤ በእግዚአብሔር ቤት ለዘለዓለም እንዲያበራ ወይም እንድታበራ ሸጋ ጠባይ እንዲኖረው ወይም እንዲኖራት አሳድጊልኝ” ይላል፡፡CLAmh 25.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents