Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር

    በጸሎት ኃይል ለመዳን የሚፈልጉ ሰዎች ሊያገኙ የሚችሉትን መድኃኒት መተው የለባቸውም፡፡ እግዚአብሔር በጥበቡ በሽታን ለማስታገስና ተፈጥሮን ለመጠገን ያዘጋጀልንን መድኃኒት መውሰድ የሃይማኖት ጉድለት አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር ተፈጥሮን ቶሎ እንድትጠግን ማድረግ ክህደት አይደለም፡፡ የኑሮን (የሕይወትን) ደንብ እንድናውቅ እግዚአብሔር ኃይል ሰጥቶናል፡፡ የተሰጠንን ዕውቀትም እንድንሠራበት ተፈቅዶልናል፡፡ በተቻለ መጠን የተፈጥሮን ሕግ በመከተል የተገኘውን ሁሉ ለጤና ማሻሻያ ማዋል ነው፡፡CLAmh 123.5

    ስለ ጤናችን እየጸለይን በዚያም ላይ እግዚአብሔር የሰጠንን በረከት በሥራ ላይ በማዋል ጤናችንን በማሻሻል በኩል ከእግዚአብሔር ጋር በኅብረት ልንሠራ እንችላለን፡፡ መድኃኒቶችን በሥራ ላይ ለማዋል የእግዚአብሔር ቃል ፈቅዶልና፡፡ የእሥራኤል ንጉስ ሕዝቅያስ ታሞ ሳለ አንድ ነቢይ ትሞታለህ የሚል መርዶ ከእግዚአብሔር ዘንድ አመጣለት፡፡CLAmh 124.1

    ንጉስ ወደ እግዚአብሔር ጮኾ ስላለቀሰ እግዚአብሔር 15 ዓመት ዕድሜ እጨምርልሃለሁ አለው፡፡ እግዚአብሔር ከተናገረው ንጉሡ ሊድን ሲችል የተለየ መመሪያ ተሰጠው፡፡ “የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተው በእባጩ ላይ ይለብጡት፤ እርሱም ይፈወሳል፡፡” ኢሣይያስ 38፡21CLAmh 124.2

    ስለበሽተኛው ከጸለይን በኋላ ምን ዓይነት ውጤት ቢመጣ በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ሊቀንስ አይገባም፡፡ ችግር ቢደርስብን መራራውን ፅዋ ወደ አፋችን ያቀረበው አምላካችን መሆኑን ሳዘነጋ በትዕግስት እንቀበል፡፡ በሽተኛው ከተረፈም የምህረት ዘይት የቀባን ጌታ ተጨማሪ ግዴታ እንደጣለብን አንዘንጋ፡፡ አሥር ለምፃሞች ሲነጹ ጌታን ተመልሶ ያመሰገነ አንዱ ብቻ ነበር፡፡ ማንም ቢሆን በክርስቶስ ፍቅር ልባቸው እንዳልተነካው እንደ ዘጠኙ ለምፃሞች አይሁን፡፡ “በጎ ሥጦታ ሁሉ ፍጹም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም ከእርሱ ዘንድ በሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ ከእርሱ ዘንድ በሌለ፤ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ” ያዕቆብ 1፡17፡፡CLAmh 124.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents