Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የስንፍና ውጤት

    ድውያንን ከሚያጠቋቸው መጥፎ ነገሮች መካከል ሥራ ፈትነት ከሁሉ የበለጠ መርገም ነው፡፤ ቀላል ሥራ ቢሠሩ አካላቸውና አእምሮአቸውን ሳይጎዳ ያስደስታቸዋል፡፡ ጡንቻን ያጠነክራል፤ ደም መዘዋወርን ይረዳል፤ ከዚያም በላይ ደካማው ሥራ ሊሠራ መቻሉን ሲያውቅ የበለጠ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ብዙ ባይሠራም እየቈየ ጉልበት ያገኛል፡፡ ቀስ በቀስ የሥራው ውጤት ሊያምር ይችላል፡፡CLAmh 101.6

    ልምምድ ሲያደርግ የበሽተኛው የምግብ መዋኃድ ይዞታ ይሻሻልለታል፡፡ ወዲያውኑ እንደበሉ ጠለቅ ያለ ጥናትን መጀመር ወይም ኃይለኛ የጉልበት ሥራ መሠራት የምግብ መዋሀድን ያደናቅፋል፡፡ ግን ከበሉ በኋላ ራስን ቀና፤ ትከሻን ቀጥ አድረጎ አጭር ጉዞ ማድረግ ይጠቅማል፡፡CLAmh 101.7

    ስለጠቃሚነቱ ብዙ ቢነገርና ቢጻፍም የሰውነት ማጠንከሪያን ትምህርት ችላ የሚሉት ጥቂቶች አይደሉም፡፡CLAmh 102.1

    አንዳንዶች የምግብ መመላለሻ ቦያቸው ስለሚዘጋባቸው ከመጠን በላይ ይወፍራሉ፤ ሌሎች ደግሞ የሚያስፈልገውን ከመጠን ያለፈ ምግብ በማስወገድ የሰውነታቸው ኃይል ስለሚያልቅ በጣም ቀጭን ይሆናሉ፡፡ ጉበት ደምን ለማጣራት ሥራ ስለሚበዛበት በሽታ ይከተላል፡፡CLAmh 102.2

    የቅምጥ ሥራ የሚያዘውትሩ ሰዎች የአየሩ ጠባይ ካመቸ ክረምት ቢሆን በጋ ውጭ እየወጡ በየቀኑ የአካል ማጠንከሪያ ልምምድ ማድረግ አለባቸው፡፡ ጡንቻዎችን በሙሉ ስለሚያንቀሳቅስ በመኪና ከመንሸራሸር ይልቅ በእግር መጓዝ ይሻላል፡፡ በእግር በምንጓዝበት ጊዜ ቀጥ ብለን ስለምንጓዝ ሳንባችን በቂ አየር ያገኛል፡፡CLAmh 102.3

    የዚህ ዓይነት የአካል ማጠንከሪያ ልምምድ ከመድኃኒት ይልቅ ለጤና ጠቃሚ ነው፡፤ ሐኪሞች በሽተኞችን አብዛኛውን ጊዜ በመርከብ እንዲጓዙ፤ ወደ ጠበል እንዲሄዱ፤ ወይም አየር ለመለወጥ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ይመክሯቸዋል፡፡ግን ከዚህ የበለጠ ውጤት የሚያገኙ የተመጣጠነ ምግብ በልክ ቢበሉ፤ በደስታ የአካል ማጠንከሪያ ልምምድ ቢሠሩ ነው፡፡ ገንዘብና ጊዜያቸውን ጤናቸውንም ጭምር ያተርፋሉ፡፡CLAmh 102.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents