Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በእግዚአብሔር ብርሃን ተመላለሱ (ተራመዱ)

    ዘወትር በእግዚአብሔር ብርሃን ተመላለሱ፡፡ ለሌሊትና ቀን የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ትጉ፡፡ ያን ጊዜ ውበቱን ለማየት ትችላላችሁ፡፡ በቸርነቱም ደስ ይላችኃል፡፡ ልባችሁ በፍቅሩ ይቃጠላል፡፡ በዘለዓለማዊ ክንዱ አቅፎ ይደግፋችኋል፡፡ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ብርሃንና ኃይል አማካይነት ካሰባችሁት በላይ ይቀናችኋል፡፡ በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ከጳውሎስ ጋር “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” ይላል፡፡ (ፊልጵስዩስ 4፡13) ፡፡CLAmh 213.1

    ያለፈው ስህተታችን ምንም ቢበዛ በእግዚአብሔር እርዳታ ልናርመው እንችላለን፡፡ ከሐዋሪያው ጋር “ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ በኋላዬ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፡፡ በክርስቶስ የሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ወደ ምልክቱ እፈጥናለሁ” ለማለት እንችላለን፡፡ (ፊልጵስዩስ 3፡13-14)CLAmh 213.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents