Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    (ነፃ) አርነት ሊያወጣን ተዘጋጅቷል

    ለፍርሃትና ለተስፋ መቁረጥ ራሱን አሳልፎ መስጠት የሚፈልግ የለም፡፡ ፈጽመህ ጠፍተሃል፤ ለመዳን ተስፋ የለህም እያለ ሠይጣን ተስፋ ያስቆርጣችሁ ይሆናል፡፡ ግን በክርስቶስ በኩል ምነጊዜም ተስፋ አላችሁ፡፡ እግዚአብሔር በራሳችን ኃይል ብቻ ታግለን እንድናሸንፍ አይተወንም፡፡ ወደ እርሱ እንድንጠጋ ይጋብዘናል፡፡ አካላችንና መንፈሳችንን የሚያደቅ ከባድ ችግር ቢወድቅብንም ነፃ ሊያወጣን ተዘጋጅቷል፡፡CLAmh 111.6

    ራሱ ሰብዓዊነትን ለብሶ ስለነበር በሰብዓዊ ፍጡር ላይ ያለው መከራ ያውቀዋል፡፡ ክርስቶስ እያንዳንዱን ሰው ከችግሩ ጋር ማወቅ ብቻ ሳይሆን የፈተናው ዓይነትና ጊዜውን ለይቶና አበጥሮ ያውቀዋል፡፡CLAmh 112.1

    በችግር ላይ ለወደቀው ለእያንዳንዱ ልጁ የምሕረትና የርዳት እጁን ዘርግቷል፡፡ ክርስቶስን ደካማው ስሜታችን ያሳዝነዋል፡፡ ችግራችንና የተደናገረንን ነገር ሁሉ ጠቅልለን በእግሩ ሥር እንድንጥለው ይጠይቀናል፡፡ ስለ ራሳችን መመራመርና የራሳችንን ስሜት ማሰላሰል ብልህነት አይደለም፡፡ ይህን ካደረግን ጠላት ፈተናና ችግር በመደርደር ድፍረታችንን ወደ ፍርሃት፤ እምነታችንን ወደ ጥርጥር ይለወጥብናል፡፡ በስሜታችን መመራት የሚያስከትለው ትርፍ ራሳችን ወደ ጥርጥርና ወደ ድንግርግር ባሕር መጣል ነው፡፡ ራሳችንን ትተን ወደ የሱስ መመልከት አለብን፡፡ ፈተና ሲደርስብን፤ ጭንቀት ድንግርግርና ጨለማ የከበበን ሲመስለን፤ ጥንት ብርሃን ወዳየንበት ቦታ በእርሱ ጠባቂነትና በፍቅሩ ሥር እንረፍ፡፡ ኃጢአት ልብህን ሊገዛ ሲታገል ወንጀል ሰውነትህን ጨቁኖ ነፍስህን፣ ሕሊናህን ሲያሰቃይ፤ መጠራጠር አዕምሮህን ሲያጨልም የክርስቶስ ጸጋ ኃጢአትን ለማራቅና ጨለማን ለመግፈፍ መቻሉን አትርሳ፡፡ ከመድኃኒታችን ጋር ስንቀራረብ በሰላም ግዛት ውስጥ እንገኛለን፡፡CLAmh 112.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents