Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከቤተሰብ ለመለየት መዘጋጀት

    በእውነተኛ ቤተሰብ ውስጥ በፍቅርና በጥበብ ካደጉ ልጆች ደስታና ጓደኝነት ፍለጋ አይንከራተቱም፡፡ ብልግና አያታልላቸውም፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የሚገኝ መንፈስ ጠባያቸውን ይገነባል፤ ከቤተሰብ ጥበቃ ወጥተው በዓለም ውስጥ ሥራቸውን በሚይዙበት ጊዜ ፈተናን ለመቋቋም የሚችል ጠባይና ደንብ ይኖራቸዋል፡፡CLAmh 36.2

    ልጆችም እንደ ወላጆቻቸው በቤተሰብ ውስጥ ሊያከናውኑት የሚገባ ዋና ተግባር አለ፡፡ ልጆች በቤተሰብ ውስጥ ዋና ክፍል እንዳላቸው መማር አለባቸው፡፡ ምግብ፣ ልብስና ፍቅር ያገኛሉ፤ ጥንቃቄም ይደረግላቸዋል፤ አባል ለሆኑበት ቤተሰብ ደስታን በማስገኘትና የሚሰጣቸውን ተግባር በመፈጸም ለሚደረግላቸው ነገር ሁሉ አመስጋኝ መሆናቸውን መግለጽ ይገባቸዋል፡፡ አንዳንድ ነገር እንዳያደርጉ በሚከለከሉበት ጊዜ ልጆ ይናደዳሉ፡፡ ይሁን እንጂ ባደጉ ጊዜ ተጠንቅቀው ስላሳደጓቸው ወላጆቻቸውን ሲያመሰግኑ ይኖራሉ፡፡CLAmh 36.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents