Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሰው ሰራሽ የከተማ ሕይወት

    የከተማ ሕይወት ሰው ሠራሽ ነው፡፡ ገንዘብ ማሳደድ ደስታ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት፣ የታይታ ምኞትና ምቾት ለማግኘት የሚደረገው የገንዘብ ማባከን፣ የብዙ ሰዎችን አንጎል ከእውነተኛው ሕይወት አርቆታል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ነገሮች በሺህ ለሚቆጠሩ የአመጽ ሥራዎች በር ከፍተውላቸዋል፡፡ እነዚህንም የአመጽ ሥራዎች ወጣቶች ሊከላከሏቸው አይችሉም፡፡CLAmh 18.2

    ለወጣቶችና ለሕፃናት በጣም አስጊና አልባሌ ከሆኑ ፈተናዎች አንዱ ደስታ የማግኘት ፍላጎት ነው፡፡ ዓመት በዓሎች እጅግ በዝተዋል፤ የጨዋታ ውድድር በሺህ የሚቆጠሩትን ይስባል፤ ደስታ ለማግኘት ያለው ዲልቃ ከትክክለኛዎቹ የሕይወት ተብባሮች አርቋቸዋል፡፡ ለተሻለ ጥቅም ሊውል የሚገባው ገንዘብ ለመደሰቻ ይባክናል፡፡ በዚህ አያያዝ ለወደፊቱ የከፋ ችግር ይጠብቀናል፤ ብዙ ቤተሰቦችም ከከተማ መውጣት ግድ ይሆንባቸዋል፡፡CLAmh 18.3

    የከተማ ኑሮ የጤና ፀር ነው፡፡ በከተማ ውስጥ ከሚገኙት መጥፎ ነገሮች ጥቂቶቹ የአየር መቆሸሽ፣ የውኃ መቆሸሽ፣ የምግብ መቆሸሽ፣ የቦታ ጥበትና የደዌ ብዛት ናቸው፡፡CLAmh 18.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents