Go to full page →

የኃጢአት ሸክም ሲቃለል CLAmh 155

የኃጢአት ሸክም ከሰውየው ትከሻ ላይ ወረደለት፤ የክርስቶስ አነጋገር የልብን ሊያውቅ መቻሉን ይገልጥልናል፡፡ ኃጢአትን የማስተስረይ ኃይሉን ማን ሊክድ ይችላል? በፍርሃት ፋንታ ድፍረትን፤ በሃዘን ፋንታ ደስታን ተካለት፡፡ የሰውየው ሥጋዊ ደዌ ለቀቀውና ሰውነቱ በሙሉ ተለወጠ፡፡ ከደስታው የተነሣ ምንም ሳይናገር ተጋድሞ ዝም አለ፡፡ ይህ አዲስ ድርጊት ሲከናወን ሰዎች ሁሉ በአድናቆት ይመለከቱ ነበር፡፡ ብዙዎችም የክርስቶስ ንግግር እነርሱንም እንደሚጠቅስ ተሰማቸው፡፡ እነርሱስ ቢሆኑ በኃጢአት አልታመሙም እንዴ? ከዚህ ሸክም ቢላቀቁ ደስ አይላቸውም? CLAmh 155.5

ፈሪሣውያን ግን በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ተወዳጅነት እንዳይቀንስባቸው አስበው በልባቸው “ይህ ሰው ለምን እንደዚህ ስድብ ይናገራል ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” አሉ፡፡ CLAmh 155.6

የሱስ ወደነርሱ ተመለከተና “ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ወይስ ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል? ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እድታውቁ” አላቸው፡፡ ወደ ሽባው ዘወር አለና ደግሞ “ተነሣና አልጋህን ተሸከም ወደ ቤትህም ሂድ” አለው፡፡ (ማቴዎስ 9፡4-5) ፡፡ CLAmh 155.7

በቃሬዛ ተሸክመው ያመጡት ድውይ እንደ ብርቱ ጎልማሳ በእግሩ ቀጥ ብሎ ቆመ፡፡ “ተነስቶም ወዲውኑ አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፤ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ፡፡” (ማርቆስ 2፡12) ፡፡ CLAmh 156.1