Go to full page →

ከየሱስ እግሮች ሥር CLAmh 155

በሽተኛውን የተሸከሙት ሰዎች ሕዝቡን አልፈው ወደ የሱስ ለመቅረብ ቢሞክሩ አልተሳካላቸውም፡፡ በሽተኛው ሥቃዩ ባሰበት፡፡ ወደ የሱስ ይህን ያህል ቀርቦ እንዴት ተስፋ ይቁረጥ? በእርሱ አሳሳቢነት ተሸካሚዎቹ ጣራውን ነድለው ከላይ ወደታች በሽተኛውን በማውረድ ወደ የሱስ አቀረቡት፡፡ CLAmh 155.1

ንግግሩ በዚህ ድርጊት ተቋረጠ፡፡ መድኅን የበሽተኛውን ገጽ ቀና ብሎ ቢመለከት በዓይኑ ሲያማጽነው ተመለከተ፡፡ CLAmh 155.2

የዚያን ሸክሙ የከበደበትን ሰው ጉጉት አወቀለት፡፡ ገና በቤቱ ሳለ በሕሊናው እንዲያሰላስል ያደረገው ክርስቶስ ነበር፡፡ በኃጢአቱ ሲጸጸት የየሱስ ኃይል እንደሚፈውሰው ሲያምን መድኅን ሰውየውን ባረከው፡፡ የሰውየው የእምነት ቅንጣት እያደገ ሲሄድና የኃጥአን ተስፋ እርሱ ብቻ መሆኑን አምኖ ወደርሱ ሊቀርብ መሆኑን የሱስ አመነ፡፡ በሽተኛውን ወደ ራሱ ያቀረበው ክርስቶስ ነበር፡፡ የሱስ በመልካም ድምፅ በሽተኛውን እንዲህ አለው፡፡ CLAmh 155.3

“አንተ ልጅ አይዞህ ኃጢአትህ ተሠረየልህ፡፡” (ማቴዎስ 9፡2) ፡፡ CLAmh 155.4