Go to full page →

በሕግ መኖር CLAmh 22

ለእሥራኤላዊቱ እናት የተነገረውን ቃል እግዚአብሔር እናት ለሆኑ ሁሉ ይናገራል፡፡ መልአኩ “ትጠንቀቅ፤ ያዘዝኋትንም ሁሉ ትጠብቅ” አለ፡፡ የሕጻኑ ጤንነት በናቱ የኑሮ ልምድ ሊመሰረት ወይም ሊፈርስ ይችላል፡፡ የምግብ አምሮቷና ስሜትዋ ሁሉ በሕግ ቁጥጥር ሥር መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር ለስዋ ልጅ የሰጠበትን የሚገባት ነገር አለ፡፡ ከልጁ መወለድ በፊት እናቲቱ ራስዋን የማትገታ (ስገብጋባ)፤ ራስዋን ብቻ የምትወድ፣ ትዕግሥት የለሽና አስገዳጅ የሆነች እንደሆነ ያው ዓይነት ጠባይ በልጁ ላይ ይታያል፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ልጆች ሊገታ የማይቻል የመጥፎ ነገር ዝንባሌ ኑሯቸው ይወለዳሉ፡፡ CLAmh 22.4

እናቲቱ ግን በሕግ የምትኖር፤ ማለት መጠነኛ፣ ራስዋን የማትወድ፣ ቸር፣ የተከበረች የሆነች እንደሆን እደዚህ ያሉትን የተከበሩ ጠባዮች ለልጅዋ ልታወርስ ትችላለች፡፡ እናት የተባለች ሁሉ አልኮሆል እንዳትጠጣ የሚያዘው ሕግ ግልጽ ነው፡፡ እናቲቱ አምሮትዋን ለማርካት ከምትጠጣው አልኮሆል እያንዳንዱ ጠብታ የልጁን የአካል፣ የአእምሮና የሞራል ጤንነት ከመጉዳቱም በላይ ፈጣሪዋን የሚያሳዝን ኃጢአት ነው፡፤ CLAmh 23.1

ብዙ መካሪዎች የናቲቱ ፍላጐት መሟላት አለበት ይላሉ፤ ይህም ማለት አንድ ዓይነት ምግብ ካስፈለጋት ምንም ጐጂ ቢሆን የፈለገችውን ያህል ሊሰጣት ይገባል ማለት ነው፡፡ ይህ ዓይነት ምክር ስህተትና ጐጂ ነው፡፡ እርግጥ ነው የናቲቱ ጤነንነት ሊናቅ አይገባም፡፡ ሁለት ሕይወት ስለምትመግብ ምኞትዋ በጥንቃቄ ሊያዝና ፍላኳትዋም በልግስና ሊሟላላት ይገባል፡፡ ይህ በሚደረግበት ጊዜ ግን ከሁሉ የበለጠ በምግብም ሆነ በሌላ ነገር የአካልንና የአዕምሮን ኃይል ሊቀንስ የሚችልን ነገር ሁሉ መተው አለባት፡፡ ራስዋን የመግታት ልመምድ እንዲኖራት በእግዚአብሔር ትእዛዝ የተቀደሰ ግዴታ ተጥሎባታል፡፡ CLAmh 23.2