Go to full page →

33—የየዕለት ሃይማኖት CLAmh 189

በእውነተኛ ክርስቲያን ንጹሕ ህይወት አማካይነት ያማረ ንግግር ከሚሰጠው መልዕክት የበለጠ ጠቃሚ ቃል ይሰማል፡፡ ሰው ከሚናገረው ይልቅ እሱነቱ የበለጠ ተሰሚነት አለው፡፡ የሱስን እንዲይዙ ተልከው የነበሩት መኰንኖች እንደ እርሱ የሚናገር ሰው አልሰማንም ብለው መሰከሩ፡፡ CLAmh 189.1

ይህ የሆነበት ምክንያት እንደ እርሱ አኗኗር የኖረ ሰው ባለመኖሩ ነው፡፡ ሕይወቱ የተለየ ባይሆን ኖሮ የዚያ ዓይነት ንግግር ሊናገር ባልቻለም ነበር፡፡ ከንጹህና ከቅዱስ፤ ከአሳዛኝና ከርኀሩኀ፤ ከታዛዥና ከእውነተኛ ልብ ስለመነጨ ቃላቱ የማሳመን ኃይል ነበራቸው፡፡ CLAmh 189.2