Go to full page →

የሱስ ቢሆን ምን ያደርግ ነበር? CLAmh 205

ሰብአዊና መለኮታዊ የሆነው ጠባዩን አጥናና” የሱስ በእኔ ቦታ ቢሆን ምን ያደርግ ነበር” ብለህ ተመራመር። ሳያስፈልግህ ትክክለገኛውን እንዳትሰራ አሳብህን ከሚያደክሙብህና ኅሊናህን ባልሆነ ነገር ከሚበክሉብህ ጋር ማህበርተኛ አትሁን፡፡ የክፋት ምልክት ካየህባቸው በመንገድ ላይ በመኪና ውስጥ ወይም በቤት ውስጥ ከምታገኛቸው እንግዶች ጋር ምንም አትሥራ፡፡ ክርስቶስ በደሙ የገዛውን ህይወትህን ለማሳመር፤ ጨዋ ለማድረግ፤ ለማሻሻል ሁልጊዜ ሞክር፡፡ CLAmh 205.2

ሁልጊዜ በህግ እንጂ በስሜት አትመራ፡፡ የተፈጥሮ ችኩልነትህን ጨዋና ትሁት ረጋ ያለ ለማድረግ ታገል፡፡ CLAmh 205.3

ፌዝና ቀልድ አታብዛ፡፡ የማይረቡ ቃላት ከአፍህ አይወጡ፡፡ የአመጽ አሳብ በልብህ አይደር፡፡ ክርስቶስን በፍፁም ልብህ ታዘዝ፡፡ አሳብህን በመልካም ነገር ላይ ብቻ አሳርፍ፡፡ ከዚያ በኋላ በክርስቶስ ፀጋ ንፁህና እውነተኛ አስተሳሰብ ይኖርሃል፡፡ CLAmh 205.4