Go to full page →

ሌሎችን የሚያበረታታ ተግባር CLAmh 206

ሌሎችን በመተቸትና በመኮነን ፋንታ “እንድድን ራሴ መጣር አለብኝ፤ ሊያድነኝ ከሚፈልገው ጋር ተባብሬ በትጋት መሥራት ይገባኛል፡፡ ከሰውነቴ ክፋትን ማስወገድ ይኖርብኛል፡፡ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን አለብኝ፤ ስህተትን ድል መንሣት ይገባኛል፡፡ ስለዚህ የተሳሳቱትን ተስፋ በማስቆረጥ ፋንታ አጽናናቸዋለሁ” በል፡፡ CLAmh 206.4

እርስ በእርሳችን መረዳዳትን ችላ እንላለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሥራ ባልደረቦቻችን ርዳታና ማበረታቻ እንደሚያስፈልጋቸው እንረሣለን፡፡ እንደማትተውዋቸውና እንደምታዝኑላቸው አረጋግጡላቸው፡፡ በፀሎታችሁ ርዷቸው፡፡ እንደምትረዷቸው ይወቁ፡፡ CLAmh 206.5

የእግዚአብሔር ልጆች ነን የሚሉ ሁሉ ወንጌላዊያን መሆናቸውን አውቀው ሰው ሳይመርጡ ማንንም ማነጋገር እንዳለባቸው አይርሱ፤ ጨዋና ባለጌ፤ ትሁትና ኩሩ፤ አማኝና ከሃዲ፤ የተማረና መሃይም፤ ድሃና ሀብታም መኖሩ አይጠረጠርም ፡፡ በዚህ ዓይነት የተለያዩትን ሰዎች ሁሉ በአንድ ዓይነት አቀራረብ ብቻ መቅረብ አይቻልም፡፡ ግን ሁሉም ርኀራኄና ፍቅር ያሻቸዋል፡፡ እርስ በእርስ በመወያየት አስተሳሰባችን ይስላል፡፡ በሰብአዊ ወንድማማችነት በመዛመዳችን አንዱ የሌላውን ድጋፍ እንፈልጋለን፡፡ CLAmh 206.6

ክርስትና በዓለም ውስጥ የሚሠራጨው በማኀበራዊ ኑሮ አማካይነት ነው፡፡ መለኮታዊ ብርሃን የተገለጠለት ሁሉ ወንድም ቢሆን ሴት መንገዳቸው ለጨለመባቸው ማብራት አለበት፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የሚካሄድ የማህበራዊ ኑሮአችን ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ መመለስ አለበት፡፡ ክርስቶስን የተቀበለ ሰው ብቻ ለግሉ የሚደሰትበት የተቀበረ መዝገብ መሆን የለበትም፡፡ ክርስቶስ በውስጣችን እንደሚፈለፍል ምንጭ ሆኖ ወደ እኛ የሚመጡትን ሁሉ ማርካት አለበት፡፡ CLAmh 207.1