Go to full page →

በእግዚአብሔር ብርሃን ተመላለሱ (ተራመዱ) CLAmh 213

ዘወትር በእግዚአብሔር ብርሃን ተመላለሱ፡፡ ለሌሊትና ቀን የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ትጉ፡፡ ያን ጊዜ ውበቱን ለማየት ትችላላችሁ፡፡ በቸርነቱም ደስ ይላችኃል፡፡ ልባችሁ በፍቅሩ ይቃጠላል፡፡ በዘለዓለማዊ ክንዱ አቅፎ ይደግፋችኋል፡፡ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ብርሃንና ኃይል አማካይነት ካሰባችሁት በላይ ይቀናችኋል፡፡ በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ከጳውሎስ ጋር “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” ይላል፡፡ (ፊልጵስዩስ 4፡13) ፡፡ CLAmh 213.1

ያለፈው ስህተታችን ምንም ቢበዛ በእግዚአብሔር እርዳታ ልናርመው እንችላለን፡፡ ከሐዋሪያው ጋር “ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ በኋላዬ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፡፡ በክርስቶስ የሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ወደ ምልክቱ እፈጥናለሁ” ለማለት እንችላለን፡፡ (ፊልጵስዩስ 3፡13-14) CLAmh 213.2