Go to full page →

8—ትምህርት ከቤተሰብ ይጀምራል CLAmh 37

ልጆቻችን በመንታ መንገድ ላይ እንደቆሙ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ራስን የመውደድና ራስን ያለመግታት ዓለማዊ ፈተናዎች እግዚአብሔር ለዳኑት የዘረጋውን መንገድ እንዲለቁ ያታልሏቸዋል፡፡ ሕይወታቸው ለበረከት ወይም ለመርገም መሆኑ የሚወሰነው በሚያደርጉት ምርጫ ነው፡፡ ብዙ ኃይል ስላላቸውና ችሎታቸውንም ለመሞከር ስለሚፈልጉ የጉልበታቸው መቀነሻ መንገድ ማግኘት አለባቸው፡፡ ንቃታቸው (ትጋታቸው) ለጥቅም ወይም ለጉዳት ሊሆን ይችላል፡፡ CLAmh 37.1

የእግዚአብሄር ቃል ትጋትን አይነቅፍም፤ ይልቁንስ በትክክል ይመራዋል፡፡ እግዚአብሔር ወጣቶች ከፍ ያለ ነገር እንዳይመኙ አያዝዝም፡፡ ሰውን የተከበረና እውነተኛ ክንውን ያለው እንዲሆን የሚያደርጉት ጠባዮች (ጥሩ ነገር የማከናወን ጥብቅ ምኞት፤ የማይበገር አሳብ፤ በኃይል መሥራት፤ ተስፋ አለመቁረጥ) መደፋፈር አለባቸው፡፡ በእግዚአብሔር ጸጋ ራስን ከመውደድ ወደተሻሉ ነገሮች መመራት አለባቸው፡፡ CLAmh 37.2