Go to full page →

እውነተኛው የብርሃን ምንጭ CLAmh 43

ብዙ ሰዎች ትምህርት ለማግኘት በመናፍቃን የተጻፉትን መጻሕፍት ማንበብ ግዴታ ነው ይላሉ፤ ይህንም የሚሉበት ምክንያት በመጽሐፎቻቸው ጥሩ ጥሩ አሳቦች ስለሚገኙ ነው፡፡ ነገር ግን የነዚህ አሳቦች ጠንሳሽ ማነው? እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ የብርሃን ሁሉ ምንጭ እርሱ ነው፡፡ እውነትን በቀላሉ ለማግኘት ስንችል ገና አንዳንድ አሳቦች እናግኝ ብለን ከስሕተት ረግረግ ውስጥ ገብተን የምንዛግጠው ለምንድን ነው? CLAmh 43.4

ከእግዚአብሔር መንግስት ጋር በመዋጋት ላይ ያሉ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ያለ ጥበብ የሚኖራቸው ለምን ይሆን? ሰይጣን የተማረው በሰማይ አደባባይ ነው፡፡ የክፉና የደግም እውቀት አለው፡፡ የከበረውን ነገር ከረከሰው ጋር ያቀላቅለዋል፡፡ ለማታለል የሚያስችው ይህ ነው፡፡ ሰይጣን የሰማያዊውን ብርሃን ልብሱን አውልቆ ስለጣለ የብርሃን መልአክ ልንለው እንችላለን ወይ? ፈታኙ በእርሱ እቅድ የሰለጠኑ፤ በእርሱ መንፈስ የተነቃቄና የሥራው ልምድ ያላቸው ወኪሎች አሉት፡፡ ከእነርሱ ጋር እንተባበር ወይ? የወኪሎቹን ሥራስ ለትምህርት አስፈላጊ ነው ብለን እንቀበል ወይ? CLAmh 43.5

የመናፍቃንን ትምህርት ለመከተል የሚጠፋው ጊዜና ጉልበት የከበረውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማስተማር ብንጠቀምበት በጨለማና በሞት ጥላ ሥር የሚኖሩ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በሕይወት ብርሃን በተደሰቱ ነበር፡፡ CLAmh 44.1

ቤተመጻሐፍት በታሪክና በሃይማኖት ማስተማሪያ ትልልቅ መጻሕፍት ተሞልተው ሳለ ምግብ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ገንዘብ እናባክናለን ብዬ አስባለሁ፡፡ በነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ልናገኘው ከምንችለው የበለጠ ከዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ልናገኝ እንችላለን፡፡ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም፤” ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡” በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡” “እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው፡፡” ዮሐ 6፡35፣51፣47፣63 CLAmh 44.2