Go to full page →

የተሟላ ኑሮ CLAmh 1

ለአንባቢያን CLAmh 2

ኑሮ ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል፡፡ ከነዚህም ዋና ዋናዎቹ ጤና፣ መልካም ቤተሰብ፣ የልብ ጓደኞ፣ የአዕምሮ ሰላምና ከእግዚአብሄር ጋር መስማማት ናቸው፡፡ የኑሮአችሁ ደረጃ ምንም ዓይነት ቢሆን እነዚህን የኑሮ ጸጋዎች ማግኘት፤ ኑሮን ልትደሰቱበት፤ የተሟላ ኑሮ ልትኖሩ ትችላላችሁ፡፡ CLAmh 2.1

ግን ሊታሰብባቸው የሚገባ ነገሮች አሉ፡፡ ኑሮ የሚያስገኛቸውን መልካም ነገሮች ለማግኘት የፈለገ ሰው ሊከተላቸው የሚገባው መሠረታዊ ደንቦች አሉ፡፡ እነዚህ በዚህ መጽሐፍ ቅስጥ የተብራሩት የኑሮ ደንቦች በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ለልዩ ልዩ ሕዝብ በቃልም በጽሑፍም አማካይነት ተዳርሰዋል፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ተጠቅመውባቸዋል፡፡ CLAmh 2.2

“የተሟላ ኑሮ” “የፈውስ አገልግለት” ከተባለ ከፍተኛ መጽሐፍ ተውጣጥቶ የተጻፈ ምርጥ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ከተጠቀሰው ትልቅ መጽሐፍ የተውጣጣ እነጂ የፊተኛው መጽሐፍ ግልባጭ አይደለም፡፡ CLAmh 2.3

በደራሲዋ መልዕክት የተጠቀሱት ምርጥ ምክሮች ምን ጊዜም ቢሆን ተፈላጊነታቸው ጊዜ የማይሽረው ነው፡፡ ደራሲዋ ስለ አልኮሆልና ስለትንባሆ፤ የወላጅ ተሰሚነት፤ ስለልጅ አስተዳደግ የሰነዘረችው አስተያየት በአሁኑ ዘመን የሳይንስና የትምህርት አቋም ሊቃውነት ከደረሱበት ምርምር ጋር የሚስማማ ነው፡፡ CLAmh 2.4

የዚህ መጽሐፍ አንባብያን ይህን መጽሐፍ በማንበባቸው የኑሮን ምርጥ ነገሮች ቁልፍ አግኝተው የተሟላ ኑሮ እንደሚኖሩ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ CLAmh 2.5

አሳታሚዎቹ CLAmh 2.6