Go to full page →

14—የቤተሰብ ልብሶች CLAmh 69

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አለባበስ ይመክራል፡፡ “እንዲሁም ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ራሳቸውን ይሸልሙ፡፡ መልካም በማድረግ እንጂ በሹርባና በወርቅ ወይም በእንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ፡፡” (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡9) ፡፡ ይህ አባባል በልብስ ከመጠን በላይ መሽቀርቀርና በቀለም ዓይነት ማምለክን፤ ወይም በብርና በወርቅ CLAmh 69.7

በአንገትና በጆሮ ጌጥ ማጌጥን ይከለክላል፡፤ በአለባበስና በጌጥ የሰውን ስሜትና ዓይን ለመማረክ የሚደረገው ማንኛውንም ጥረት እግዚአብሔር በቃሉ አውግዞታል፡፡ ልብሳችንም ዋጋው ውድ መሆን አያስፈልገውም፡፡ CLAmh 70.1

ገንዘብ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን አደራ ነው፡፡ ጉጉታችንና የልባችን ኵራት የምናረካበት የግል መሣሪያችን አይደለም፡፤ ገንዘብ ለእግዚአብሔር ሰዎች የሚታደለው ለተራቡ ምግብ፣ ለታረዙ ልብስ እንዲሆን ነው፡፡ ለተጐሳቆሉት መጠገኛ፤ ለታመሙት መታከሚያ፤ ለምስኪኖች የወንጌል ማዳረሻ መሣሪያ ነው፡፡ ለታይታ የሚባክነውን ገንዘብ በሚገባ ብትሠራበት ያዘኑትን ሰዎች ሊያስደስት ይችላል፡፡ CLAmh 70.2

የክርስቶስን ኑሮ አስታውስ፡፡ ባሕርዩን ተመራመርና ራስህን በመካድ ለድርጊቱ ተባባሪ ሁን፡፡ የክርስቲያን ዓለም በተባለው አካባኪ የተራቡትን ለመመገብ፤ የታረዙትን ለማልበስ የሚበቃ ገንዘብ በጌጣጌጥና በውድ ልብስ ይባክናል፡፡ ድኆችንና የተቸገሩትን መርዳት የሚገባው ገንዘብ (በፋሽን) በታይታ ያልቃል፡፡ እነዚህ አጉል ድርጊቶች ለዓለም ወንጌል እንዳይዳረስ ይከለክላሉ፡፡ የክርስትና ትምህርት ሳያገኙ የሚሞቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ አገር አሕዛብ ስለመዳን አልተማሩም፡፡ CLAmh 70.3