Go to full page →

የአደጋ ብዛት ጠንቅ CLAmh 78

በመጠጥ ጠንቅ የሚደርሱትን የየእለቱን አደጋዎች ተመልከቱ፡፡ በባቡር መንገድ ላይ ያለውን ምልክት አንዳንድ ነጂዎች ችላ ይሉታል፤ ወይም በተሳሳተ ትርጉም ያስተውሉታል፡፡ ባቡሩ መንገዱን ይቀጥልና ግጭት ይፈጠራል፡፡ ወይም ሀዲዱን ለቆ ገደል ይገባና ተሣፋሪዎቹ በሙሉ እርግፍ ይላሉ፡፤ ነገሩ ሲመረመር ከባድ ኃላፊነት የተጣለበት ሰው በመጠጥ ኃይል ስለተመረዘ አደጋው መድረሱ ይታወቃል፡፡ አንድ ሰው መጠጥ እስከምን ደረጃ ድረስ ቢጠጣ ነው በሰው ሕይወት ላይ ያለበትን ኃላፊነት ያለ ጉድለት ሊያጠናቅቅ የሚችል? ሥራውን በሚገባ ለማካሄድ ከፈለገ ፈጽሞ አለመንካት ይበጀዋል፡፡ CLAmh 78.4

ቢራ፣ ጠጅ፣ የጠንካራ መጠጥ ያህል ሊያሰክሩ ይችላሉ፡፡ ቀለል ያሉት መጠጦች የጠንካራ መጠጥን አምሮት ይፈጥና የጠጭነት ሱስ ይተከላል፡፡ መጠነኛ መጠጥ ሰዎች ስለ ሰካራምነት የሚሠለጥኑበት ትምህርት ቤት ነው፡፡ ነገሩ ውስጥ ለውስጥ ስለሚሠራ ጠጭው ሳይገነዘበው የመጠጥ ተገዥ ሆኖ ያገኘዋል፡፡ CLAmh 78.5

በጨጭነት ደረጃ የማይጠረጠሩ ሰዎች በስካር ጥላ ሥር መገኘታቸው ያስደንቃል፡፡ የትኩሳት በሽታ ያጠቃቸዋል፤ ወላዋይ ይሆናሉ፤ ያልተደላደለ አስተሳሰብ ይኖራቸዋል፡፡ በሰላም አለን ብለው ሲያስቡ መጠጡን ካላቋረጡ ያላቸው የመከላከያ ኃይል ያከትማል፡፡ ደንብና ሥርዓትን ጥሰው ከሕግ ውጭ ይሆናሉ፡፤ ጨክነው ቆረጥን ቢሉ አይሳካላቸውም፤ አመዛዝነው ፍላጎታቸውን እንግታ ቢሉም አሳባቸው ውድቅ ይሆናል፡፡ CLAmh 79.1