Go to full page →

የቃና ዘገሊላ ጠጅ CLAmh 79

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሰክር የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ፈጽሞ አይፈቅድም፡፡ የሱስ በቃና ዘገሊላ ከውኃ የጣለው ጠጅ ከንጹሕ የወይን ፍሬ የተጠመቀ የማያሰክር ጭማቂ ነበር፡፡ CLAmh 79.2

“በመጥመቂያው ውስጥ ያለ በተሀ ጠጅ ነበር፡፡” መጽሀፍ ቅዱስ “በረከት በእርሱ ላይ አለና አታጥፉት” ብሎ ይናገርለታል፡፡ CLAmh 79.3

በብሉይ ኪዳን “የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፤ በዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም” ብሎ እሥራኤሎችን የመከረ ክርስቶስ ራሱ ነበር፡፡ (ምሳሌ 20፡1) ራሱም የሚያሰክር መጠጥ ለሕዝብ አላቀረበም፡፡ ሰይጣን አስተሳሰባቸውን የሚያደንዝ፣ መንፈሳዊ ስሜታቸውን የሚያፈዝ ነገር እንዲያደርጉ ሰዎች ይፈትናቸዋል፡፡ ክርስቶስ ግን የሥጋ ፈቃዳችን እንድንቆጣጠረው ያስተምረናል፡፡ በሰዎች ፊት ፈተና የሚሆን ነገር ፈጽሞ አያቀርብም፡፡ ኑሮው በሙሉ ራስን የመቆጣጠር አርኣያነት ነው፡፡ ሰው ሊደርስበት የሚችለውን ከፍተኛ ፈተና ዓርባ ቀን ጾሞ የተጋፈጠው የምግብ ፍላጎትን ኃይል ለማሸነፍ ነበር፤፤ CLAmh 79.4

ዮሐንስ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ እንዳይቀምስ ያስጠነቀቀ ክርስቶስ ራሱ ነበር፡፡ ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ለማኖዓ ሚስት የተናገረም ራሱ ነበር፡፡ ክርስቶስ ያስተማረውን ራሱ አያፈርስም፡፡ ለሰርገኛው ሁሉ ያቀረበው በተሀ ጠጅ አያሰክርም ነበር፡፡ ለመጀመሪያው የጌታ ራት (ቅዱስ ቁርባን) የሱስና ደቀመዛሙርት የቀመሱት ወይንም ተመሳሳይ ነበር፡፤ ያም የጌታ ደም ምሳሌ ነበር፡፡ ያ ቅዱስ ሥነ ሥርዓት ሥጋን አለምልሞ ነፍስን እንዲጠግን የታሰበ ነው፡፡ የክፋት ምንጭ የሆነ ነገር ከዚህ ቅዱስ ሥነ ሥርዓት ጋት ግንኙነት ሊኖረው አይገባም፡፡ CLAmh 79.5

መሻትን አለመግዛት የሚጀመረው አብዛኛውን ቢዜ በቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡ ባልተገባና በከባድ ምግብ ምክንያት የምግብ ማዋሃጃው የአካል ክፍል ይጎዳል፡፡ ተጨማሪ ከባድ ምግብ የማግኘት ፍላጎት ይፈጠራል፡፡ CLAmh 79.6

አካልን የሚያነቃቃ ምግብ ወይም መጠጥ ፍላጎት እያየለ ሲሄድ መቋቋም ያስቸግራል፡፡ አካላችን በመጠኑ መርዝ ይሰራጭበታል፤ እየተዳከመ እንደሄደ መጠን ፍላጎታችን በማየል ወደ ሱስነት ይለወጣል፡፡ አንዱ ስሕተት ሌላ ስሕተትን ይወልዳል፡፡ አንዳንዶች አልኮሆል በምግብ ጠረጴዛቸው ላይ ባያቀርቡም በገበታው የቀረበው ምግብ የጠንካራን መጠጥ አምሮት የሚያስከትል ከሆነ ፈተናውን መቋቋም ያቅታቸዋል፡፡ CLAmh 80.1

መጥፎ ያመጋገብና የመጠጥ ልምድ ጤናን ይበድላል፤ የሰካራምነትን መንገድም ይጠርጋል፡፡ CLAmh 80.2