Go to full page →

ራስን የመካድ ጥቅም Amh2SM 196

የሕትመት ቢሮ ሌሎች የማተሚያ ቤቶች በሚመሩባቸው መርሆዎች መመራት እንደሌለበት እንዳይ ተደርጌያለሁ፤ መሆን ያለበት በማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ስርዓት ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያለው እያንዳንዱ ሰው እውነተኛ ሚስዮናዊ በመሆን ቢሮውን ወደ መኖር ባመጡት መርሆዎች ላይ መስራት አለበት፡፡ ሁሉም ሰራተኞች ራስን በመካድ ተለይተው መታወቅ አለባቸው፡፡ . . . Amh2SM 196.1

በቢሮ ውስጥ ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን በመካድ ተለይተው የሚታወቁና ለሰራተኞች ሁሉ ምሳሌ የሚሆኑ መሆን አለባቸው፡፡ ቢሮ የተፈጠረው ራስን በመካድ ስለነበር ያው መንፈስ መታየትና መቀጠል አለበት፡፡ ትልቁ ዓላማ በእይታ ውስጥ መቆየት አለበት፡፡ እርሱም ሚስዮናዊ ሥራ ሲሆን ሚስዮናዊ መንፈስ የሌላቸው ሰዎች በሥራው መቀጠል የለባቸውም፡፡--Letter 5, 1892. Amh2SM 196.2