Go to full page →

ምዕራፍ 22—ለሰራተኞች ትምህርት የሚደረግ የገንዘብ እገዛ Amh2SM 208

ተስፋ የሚጣልባቸውን ወጣቶች እርዱ Amh2SM 208

የእውነትና የጽድቅ ፍቅር እንደ የሕክምና ሚስዮናውያን፣ እንደ የጽሁፍ ወንጌላዊያን፣ እና እንደ ወንጌላዊያን ለእግዚአብሔር ሥራ ራሳቸውን እንዲለዩ በመምራት አስገዳጅ ተጽእኖ እንዳለው የሚታይባቸውን ወጣቶች መርዳት የወንጌል ሥራ ክፍል መሆን አለበት፡፡ ይህ ሥራ ወደ ፊት እንዲቀጥል ገቢ መገኘት አለበት፡፡ እርዳታው የተሰጣቸው ሰዎች ሕመምተኞችንና በሥቃይ ውስጥ ያሉትን ለማገልገል ይሂዱ፡፡ ይህ ሥራ በእርግጠኝነት በኃጢአት የታመሙ ነፍሳት የጊልአድን ቅባት እንዲያገኙ መንገድ ይከፍታል፡፡--Manuscript 35, 1901. Amh2SM 208.1