Go to full page →

እርዳታ የተደረገላቸው የመጀመሪያዎች የሕክምና ተማሪዎች Amh2SM 208

ሶስት ተስፋ የሚጣልባቸውን ወጣቶች ዝቅተኛ ከሆነ ሥራቸው በማንሳት በሕክምና መስመር ትምህርት እንዲያገኙ ለእያንዳንዳቸው አንድ ሺህ ዶላር እንዲሰጣቸው በማድረግ ላይ እኔና ባለቤቴም ተባብረን ነበር፡፡ ይህ እግዚአብሔር በባለቤቴ አእምሮ ውስጥ ያስቀመጠው ምርጫ ነበር፡፡ እነዚህን ሶስት ወጣቶች ለመምረጥ እግዚአብሔር ብርሃን የሰጠ ሲሆን እነርሱ ደግሞ ራሳቸውን ለሕክምና ሥራ አሳልፈው ሊሰጡ ነበር፡፡--Letter 322, 1905. Amh2SM 208.2