Go to full page →

ቀጣይነቱ አነስተኛ የሆነ አልፊ ሥራ Amh2SM 230

ውድ ወንድሜ ኤስ ኤን ሃስከል፣

ማድረግ ከምትችለው በላይ እንዳትሰራ አደፋፍርሃለሁ፡፡ ለራስህ እረፍት መስጠት እንድትችል ቀጣይነት የሌለው፣ አድካሚ ያልሆነ ሥራ መሥራት አለብህ፡፡ በቀን ጊዜ መተኛት አለብህ፡፡ ያኔ በደንብ ማሰብ ትችላለህ፣ ሀሳቦችህ የጠሩና ቃላቶችህም አሳማኝ ይሆናሉ፡፡ መላው አንተነትህ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ስለመኖሩ እርግጠኛ ሁን፡፡ መንፈሳዊ ብርሃን እንዲኖርህ መንፈስ ቅዱስን ተቀበልና በእርሱ ምሪት እግዚአብሔርን እወቅ፡፡ እግዚአብሔር የሚያዝህን በማድረግ እርሱ ወደሚመራህ ሂድ፡፡ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፣ እርሱም ኃይልህን ያድሳል፡፡ Amh2SM 230.3

ግን ቀጣይነት ያለው አድካሚ ሥራ እንድንሰራ ከአንተና ከእኔ አይጠበቅብንም፡፡ እርሱ የሚፈልግብንን ነገር ያለማቋረጥ ለእርሱ አሳልፈን መስጠት አለብን፣ እሱም ቃል ኪዳኑን ያሳየናል፡፡ «እግዚአብሔር ለሚፈሩት ቃል ኪዳኑን ያስታውቃቸዋል» (መዝ. 25፡ 14)፡፡ ስለ እግዚአብሔር አብ እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሚስጢር የበለጠ ጥልቅ ትምህርት ይሰጠናል፡፡ በውበት ስለተጎናጸፈው ንጉሥ ራዕይ እናያለን፣ ለእግዚአብሔር ሕዝብ የቀረላቸው እረፍት በፊታችን ይከፈታል፡፡ ሰሪዋና ፈጣሪዋ እግዚአብሔር ወደ ሆነው ከተማ፣ ለረዥም ጊዜ ስናወራ ወደነበረው ከተማ በቅርቡ እንገባለን፡፡ Letter 78, 1906. Amh2SM 230.4