Go to full page →

የማፈግፈግ ሀሳብ የለም Amh2SM 239

ሐምሌ 10 ቀን 1892 ዓ.ም፡፡ እሳት እንድታነድልኝና ልብሴን እንድለብስ እንድትረዳኝ ኤሚሊን ቀሰቀስኳት (ሚስስ ኤሚሊ ካምቤል የሚስስ ኋይት አብሮ ተጓዥ እና ፀሐፊ ነበረች)፡፡ ከተለመደው የተሻለ የሌሊት እረፍት ስለነበረኝ ጌታን አመሰግናለሁ፡፡ ከእንቅልፍ የነቀሁባቸውን ሰዓታት ለጸሎትና ለማሰላሰል አውላቸዋለሁ፡፡ ወደ ጤንነት የመመለስ በረከትን የማልቀበለው ለምንድን ነው? የሚል ጥያቄ በግድ ወደ እኔ ይመጣል፡፡ እነዚህን ረዥም በሕመም ያሳለፍኳቸውን ወራት ወደ አውስትራሊያ በመምጣቴ እግዚአብሔር እንዳልተደሰተ አድርጌ ልተርጉመውን? እንደዚህ ለማድረግ አልደፍርም ብዬ በቁርጠኝነት መልስ እሰጣለሁ፡፡ ገና አሜሪካ ሳለሁ በእኔ እድሜ እና ብዙ ከመስራት የተነሳ ደክሜ ሳለሁ እንደዚህ በጣም ሩቅ ወደሆነ አገር እንድሄድ እግዚአብሔር አልጠየቀኝም ብዬ ያሰብኩባቸው ጊዜያቶች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ለራሴ ግልጽ የሆነ ብርሃን ባልተሰጠኝ ጊዜ ሁሉ ለማድረግ እንደሞከርኩት ሁሉ የተከተልኩት የጄኔራል ኮንፍራንስን ድምጽ ነበር፡፡ ወደ አውስትራሊያ መጥቼ እንዳገኘሁት አማኞቹ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሆኖ ነበር፡፡ እዚህ ከደረስኩ በኋላ ከዚህ በፊት በሕይወቴ ዘመን እሰራ እንደነበረ ሁሉ ለሳምንታት በትጋት ሰራሁ፡፡ የግል ቅድስናን አስፈላጊነት በተመለከተ እንድናገር ቃላት ተሰጥተውኝ ነበር፡፡. . . . Amh2SM 239.2

ያለሁት በአውስትራሊያ ሲሆን ያለሁትም እግዚአብሔር እንድሆን በሚፈልግብኝ ቦታ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ሥቃይ ድርሻዬ ስለሆነ የማፈግፈግ ሀሳብ የለኝም፡፡ ኢየሱስ የእኔ እንደሆነ እና እኔም ልጁ እንደሆንኩ የተባረከ መተማመኛ ተሰጥቶኛል፡፡ ጨለማው በጽድቅ የፀሐይ ጮራ ተወግዷል፡፡ እኛ የሚደርስብንን ሥቃይ ተሰቃይቶ ከሚያውቅ በስተቀር እኔ እየተሰቃየሁ ያለሁበትን ሥቃይ መረዳት የሚችል ማን ነው? በእኛ ድካም ስሜት ተነክቶ ከሚያውቅ እና የሚፈተኑትን እንዴት እንደሚያግዝ ከሚያውቅ ከእርሱ በቀር ለማን እናገራለሁ? Amh2SM 239.3

ጤንነቴ እንዲመለስልኝ ከልቤ ስጸልይ፣ እና ጌታ መልስ ሳይመልስ ሲቀር መንፈሴ በውስጤ ሊዝል ይላል፡፡ በዚያን ጊዜ ውዱ አዳኝ የእርሱን መገኘት እንድገነዘብ ያደርገኛል፡፡ በራሱ ደም የገዛሽን ልትታመኝበት አትችይምን? ይለኛል፡፡ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፡፡ ያኔ ነፍሴ በመለኮታዊ መገኘት ይረካል፡፡ በእግዚአብሔር መገኘት ፊት እንደሆንኩ እስኪሰማኝ ድረስ ከራሴ ተለይቼ ወደ ላይ ከፍ ተደረግኩ፡፡ --Manuscript 19, 1892. Amh2SM 240.1