Go to full page →

“ጌታ ያበረታኛል” Amh2SM 239

ሐምሌ 7 ቀን 1892 ዓ.ም፡፡ ጠቃሚ የሆኑ ደብዳቤዎችን እንድጽፍ ጌታ በጸጋው ያበረታኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ወንድሞች ለምክር ወደ እኔ ይመጣሉ፡፡ ይህ አሰልቺ የሆነ ሥቃይ ለእግዚአብሔር ክብር እንደሆነ ጽኑ የሆነ እርግጠኝነት ይሰማኛል፡፡ አላጉረመርምም፤ ሌሊት ስነቃ፣ ኢየሱስ እየተመለከተኝ ያለ ይመስለኛል፡፡ የኢሳይያስ 51ኛው ምዕራፍ ለእኔ እጅግ የከበረ ነው፡፡ እርሱ ሸክማችንን ሁሉ ይሸከምልናል፡፡ ይህን ምዕራፍ የማነበው በእርግጠንነት ስሜትና በተስፋ ነው፡፡--Manuscript 19, 1892. Amh2SM 239.1