Go to full page →

የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ለመምረጥ ዕጣ መጣል Amh2SM 328

ዕጣ በመጣል ላይ እምነት የለኝም፡፡ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ተግባራት በተመለከተ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚል ግልጽ ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ፡፡ Amh2SM 328.5

በ----ላሉት የቤተ ክርስቲያን አባላት እንዲህ ማለት እወዳለሁ፣ «መጽሐፍ ቅዱሶቻችሁን በብዙ ጸሎት አንብቡ፡፡ ሌሎችን ለማዋረድ አትሞክሩ፣ ነገር ግን ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት አዋርዱ፡፡ ከእርስ በርሳችሁ ጋር በእርጋታ ተነጋገሩ፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ለመምረጥ ዕጣ መጣል በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ውስጥ የለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ለመምረጥ ሀላፊነት የሚሰማቸው ሰዎች ይሰብሰቡ፡፡” Letter 37, 1900. Amh2SM 328.6