Go to full page →

ለብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት የሚቀርብ ጥሪን በተመለከተ የተሰጠ ብርሃን Amh2SM 334

ሕሊናችን በሚያዝ ሁኔታ ሕዝባችን የአምልኮ ነጻነትን እንዲያገኝ መከተል ያለብን መንገድ የቱ ነው ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፡፡ ይህ ጉዳይ እምነታችንን መካድ ወይም መታመናችንን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ ያለማድረግ ማረጋገጫ ይሆን ይሆን በማለት ለተወሰነ ጊዜ የነፍሴ ሸክም ሆኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ከብሔራዊ ውትድርና ጥሪ እና ከሌሎች ነገሮች ጋር ተመሳሳይነት ስላላቸው ነገሮች ከዚህ በፊት እግዚአብሔር ያሳየኝን ነገሮች ወደ አእምሮዬ አመጣለሁ፡፡ እግዚአብሔርን በመፍራት እናገራለሁ፣ ሕዝባችን እንዲሸከም እየመጣ ያለውን ጫና ለመመከት እያንዳንዱን ኃይል መጠቀም ትክክል ነው፡፡ Amh2SM 334.5