Go to full page →

ዓለም እየተመለከተ ነው Amh2SM 386

ነቢዩ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቅን ሕዝብ «አስደናቂ ሰዎች” በማለት ይገልጻል፡፡ ከዓለም የተለየን ሕዝብ መሆን አለብን፡፡ የዓለም ዓይኖች እየተመለከቱን ስለሆነ በማናውቃቸው በብዙ ሰዎች በመታየት ላይ እንገኛለን፡፡ እኛ እንደምናምን ስለምንናገራቸው አስተምህሮዎች የሆነ ያህል የሚያውቁ ሰዎች እምነታችን በባሕርያችን ላይ ያለውን ተጽእኖ እየተመለከቱ ናቸው፡፡ ምን ዓይነት ተጽእኖ እንደምናሳድርና እምነት በሌለው ዓለም ውስጥ ራሳችንን እንዴት እንደምንመራ ለማየት እየጠበቁ ናቸው፡፡ የሰማይ መላእክት እየተመለከቱን ናቸው፡፡ «በዓለምና በመላእክት በሰዎችም የምንታይ ሆነናል» (1 ቆሮ. 4፡9)፡፡ The Review and Herald, June 18, 1889. Amh2SM 386.1