Go to full page →

የእግዚአብሔር ሕዝብ የወደፊት ሁኔታ Amh2SM 386

ሕዝባችን ልብ ብሎ ለማየት የማይበቃ እጅግ አነስተኛ ተደርጎ ታይቷል፣ ነገር ግን ለውጥ ይመጣል፤ አሁን እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ናቸው፡፡ አሁን የክርስቲያን ዓለም የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቅ ሕዝብ የግድ ወደ መታየት እንዲመጣ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሰብዓዊ መነሻ ላላቸው መላ-ምቶችና ሀሰተኛ አስተምህሮዎች በማለት በየቀኑ የእግዚአብሔርን እውነት መጨቆን አለ፡፡ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሚሆኑ ህሊናዎችን ባሪያ ለማድረግ በእግራቸው እየቆሙ ያሉ እቅዶችና እንቅስቃሴዎች አሉ፡፡ ሕግ አውጪ ኃይሎች የእግዚአብሔርን ሕግ ይቃወማሉ፡፡ እያንዳንዱ ነፍስ ይፈተናል፡፡ እንደ ሕዝብ ጠቢባን መሆንና በቃልና በምሳሌ ያንን ጥበብ ለልጆቻችን ማካፈል ይጠበቅብናል፡፡ የእምነታችን እያንዳንዱ አቅጣጫ ይመረመራል፡፡ ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ካልሆንን፣ ካልተመሰረትን፣ ካልጠነከርን፣ ካልፀናን፣ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ጥበብ ከአቅማችን በላይ ይሆንብናል፡፡ Letter 12, 1886. Amh2SM 386.2