Go to full page →

እንደ አንድ ቤተሰብ ሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ Amh2SM 487

መንፈስ ቅዱስ በሰብአዊ አእምሮ ላይ ሲሰራ በሰው እና በመሰል ሰው መካከል የሚኖሩ ጥቃቅን ቅራኔዎችና ክሶች ይወገዳሉ፡፡ የጽድቅ ፀሐይ ብሩህ ጮራዎች በአእምሮና በልብ ክፍሎች ውስጥ ያበራሉ፡፡ እግዚአብሔርን ስናመልክ በደሃና በሃብታም፣ በነጭና በጥቁር መካከል ልዩነት አይኖርም፡፡ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ እንደ ወንድማማች ሆነን ነው፡፡ ወደ ተሻለው አገር፣ ያውም ወደ ሰማያዊ መንግሥት እየተጓዝን ያለን መንገደኞችና እንግዶች ነን፡፡ በዚያ ቦታ ኩራት ሁሉ፣ ክስ ሁሉ፣ ራስን ማታለል ሁሉ ለዘላለም ወደ ፍጻሜ ይመጣሉ፡፡ እያንዳንዱ ጭንብል ይወገድና «እርሱን በእርሱነቱ» እንመለከታለን፡፡ በዚያ ቦታ ዝማሬያችን የሚያነሳሳ መልእክት ያለው ይሆንና ምስጋናችንና ውዳሴያችን ወደ እግዚአብሔር ይወጣል፡፡--Review and Herald, Oct. 24, 1899, p. 677. Amh2SM 487.2