Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    እንደ አንድ ቤተሰብ ሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ

    መንፈስ ቅዱስ በሰብአዊ አእምሮ ላይ ሲሰራ በሰው እና በመሰል ሰው መካከል የሚኖሩ ጥቃቅን ቅራኔዎችና ክሶች ይወገዳሉ፡፡ የጽድቅ ፀሐይ ብሩህ ጮራዎች በአእምሮና በልብ ክፍሎች ውስጥ ያበራሉ፡፡ እግዚአብሔርን ስናመልክ በደሃና በሃብታም፣ በነጭና በጥቁር መካከል ልዩነት አይኖርም፡፡ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ እንደ ወንድማማች ሆነን ነው፡፡ ወደ ተሻለው አገር፣ ያውም ወደ ሰማያዊ መንግሥት እየተጓዝን ያለን መንገደኞችና እንግዶች ነን፡፡ በዚያ ቦታ ኩራት ሁሉ፣ ክስ ሁሉ፣ ራስን ማታለል ሁሉ ለዘላለም ወደ ፍጻሜ ይመጣሉ፡፡ እያንዳንዱ ጭንብል ይወገድና «እርሱን በእርሱነቱ» እንመለከታለን፡፡ በዚያ ቦታ ዝማሬያችን የሚያነሳሳ መልእክት ያለው ይሆንና ምስጋናችንና ውዳሴያችን ወደ እግዚአብሔር ይወጣል፡፡--Review and Herald, Oct. 24, 1899, p. 677.Amh2SM 487.2