Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በታጠፈ ጉልበት

    እግዚአብሔርን ለማምለክ ስትሰበሰቡ እርግጠኛ ሁኑና ጉልበታችሁን በፊቱ አንበርክኩ፡፡ ይህ ድርጊት መላው ነፍስ፣ አካልና መንፈስ ለእውነት መንፈስ ተገዥ መሆናቸውን ይመስክር፡፡ ይህን በተመለከተ ምሳሌ እንዲሆንለትና መመሪያ ለማግኘት ቃሉን በቅርበት የመረመረ ማን ነው? በአሜሪካና በውጭ አገሮች ባሉ ትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ እንደ መምህራን የምንተማመንባቸው እነማንን ነው? ተማሪዎች ለአመታት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ወደ አገሮቻቸው ሲመለሱ ለእግዚአብሔር መስጠት ስላለባቸው አክብሮት፣ ክብርና ስግደት የተዛባ አስተሳሰብ ይዘው ይመለሱ ይሆን? አዛውንትን፣ ልምድ ያላቸውን ሰዎች፣ እድሜያቸውን በሙሉ ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን የተመረጡ የጌታ አገልጋዮችን የማክበር ግዴታ እንደሌለባቸው ይሰማቸው ይሆን? በአሜሪካም ሆነ በማንኛውም ሌላ ቦታ ትምህርታቸውን የሚከታተሉትን ሁሉ አክብሮት የጎደለው መንፈስ አይኑራችሁ ብዬ እመክራለሁ፡፡ በምድር ላይ በሚኖሩት ሁሉ ላይ በቅርብ ሊመጣ ያለውን ፈተና መቋቋም የሚችል ገጣሚ ባሕርይ ማግኘት እንድትችሉና ሌሎችን ማስተማር እንድትችሉ ለራሳችሁ ምን ዓይነት ትምህርት እንደሚያስፈልጋችሁ ማስተዋላችሁን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ትክክለኛ ከሆኑ ክርስቲያኖች ጋር ተወዳጁ፡፡ አስመሳይ የሆኑ መምህራንንም ሆነ ተማሪዎችን አትምረጡ፣ ነገር ግን ጥልቅ የሆነ ቅድስና ያላቸውን፣ በእግዚአብሔር ነገሮች ላይ መረጃ ያላቸውን ሰዎች ምረጡ፡፡Amh2SM 314.2

    አደገኛ የሆነ ዘመን ውስጥ እየኖርን ነን፡፡ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ሕግጋትን የምንጠብቅ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነን ባይ ናቸው፤ ነገር ግን የመንፈሳዊነትን መንፈስ በማጣት ላይ ናቸው፡፡ እግዚአብሔርን የማክበር መንፈስ ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው በቅድስናና በእምነት ሆነው በፍርሃት፣ በራሳቸው ሳይሆን በአማላጅ አማካይነት መቅረብ እንዳለባቸው ያስተምራል፡፡ በመሆኑም ሰው በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ተጠብቋል፡፡ ሰው በጉልበቱ በመንበርከክ የፀጋ ተገዥ በመሆን በምህረት ግርጌ በመማጸን መቅረብ አለበት፡፡ ከእግዚአብሔር እጅ እለታዊ ምህረትን ሲቀበል ሁልጊዜ በልቡ አመስጋኝ መሆንና ለእነዚህ በመልካም ሥራ ላልተገኙ በጎነቶች አመስጋኝነቱን በምስጋናና በውዳሴ ቃላቶች መግለጽ አለበት፡፡ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ መላእክት መንገዱን ይጠብቁ ስለነበር እነርሱ ያስመለጡትን አብዛኞቹን ወጥመዶች አላያቸውም ነበር፡፡ ለዚህ ሞግዚትነቱና በፍጹም በማይተኙና በማያንቀላፉ ዓይኖቹ ስለሚያደርገው ጥበቃ በእያንዳንዱ ጸሎት ውስጥ እግዚአብሔር ያደረገለትን አገልግሎት መገንዘብ አለበት፡፡Amh2SM 314.3

    ረዳተ ቢስነት ሲሰማቸው እና በየዕለቱ ለሚያስፈልጓቸው ነገሮች ሁሉም በእግዚአብሔር መደገፍ አለባቸው፡፡ ትሁት፣ ንቁና የሚጸልዩ መሆን አለባቸው፡፡ በአመስጋኝነት እና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ልባዊ ፍቅር በመግለጽ ምስጋናና ውዳሴ ከአፋቸው ማፍለቅ አለባቸው፡፡Amh2SM 315.1

    በታማኞች ስብሰባ እና ጉባኤ ኃያሉን አምላክ ማመስገን አለባቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አስፈላጊ የሆነ ግንኙነት እንዳላቸው የሚሰማቸው ሰዎች ሁሉ የእርሱን ፍቅር፣ ምህረት እና መልካምነት በመግለጽ በጌታ ፊት ምስክሮች ሆነው መቆም አለባቸው፡፡ ልባቸው በእግዚአብሔር ፍቅር እየተቃጠለ፣ ከናፍሮቻቸው የእግዚአብሔርን ፍቅር በቅዱሳን ጉባኤ ለመግለጽ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቦታ ምስክሮቹ ለመሆን ለእርሱ ክብር የተቀደሱ ሆነው ቃላቶቻቸው እውነተኛ፣ ቀላል፣ ልባዊ፣ ማስተዋል ያለባቸው ይሁኑ፡፡ የምድር ኗሪዎች እርሱ አምላክ፣ ብቸኛው እውነተኛና ሕያው አምላክ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡Amh2SM 315.2

    በአክብሮትና ፈሪሀ-እግዚአብሔር ባለበት የፍቅር አምልኮ ወደ እግዚአብሔር እንዴት መምጣት እንደሚቻል ትክክለኛ እውቀት መኖር አለበት፡፡ ለፈጣሪያችን የሚገባውን አክብሮት አለመስጠት እየጨመረ ነው፣ ታላቅነቱንና ግርማዊነቱን አለመቀበልም እየጨመረ ነው፡፡ ነገር ግን በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት እግዚአብሔር እየተናገረን ነው፡፡ ድምጹን በማዕበልና በሚንጎደጎድ መብረቅ ውስጥ እንሰማለን፡፡ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በውኃ መጥለቅለቅ እና በዓይናችን ፊት እያየን እየጠራራጉ ባሉ አጥፊ ኃይሎች ውስጥ እሱ እንዲከሰቱ የፈቀዳቸውን መቅሰፍቶች እንሰማለን፡፡ እግዚአብሔር እሱን ለማወቅ እምቢ ላሉት ቤተሰቦች አንዳንድ ጊዜ በአውሎ ንፋስና በወጀብ፣ አንዳንድ ጊዜም ለሙሴ እንደተናገረ ፊት ለፊት ይናገራል፡፡ እንደገና ፍቅሩን ለሚታመንበት ትንሽ ልጅም ሆነ ለጃጀ አዛውንት በለሆሳስ ይናገራል፡፡ ምድራዊ ጥበብ የማይታይ ነገርን እንደ ማየት ያለ ጥበብ ነው፡፡Amh2SM 315.3

    ዓለቶችን ከቦታቸው የሚያንቀሳቅሰውን አውሎ ንፋስንና ወጀብን ተከትሎ የሚመጣው ትንሽ ጸጥ ያለ ድምጽ ሲሰማ እግዚአብሔር እጅግ ቅርብ ስለሆነ ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍኑ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ መሸሸጊያቸው ስለሆነ ራሳቸውን በእርሱ ውስጥ ይሰውሩ፡፡ ጌታ ለባሪያዎቹ የሚለውን ለመስማት የሚፈልግ ትሁት ሰው ዝቅ ባለ አመለካከት ሲጠብቅ ሳለ በአለቱ ላይ የነበረው ስንጥቅ በተወጉ በኢየሱስ እጆች ተሰውሯል፡፡ Manuscript 84b, 1897.Amh2SM 316.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents