Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በጽዮን ተመቻችተው ያሉት መቀስቀስ አለባቸው

    እውነትን ተሸክመው ክብደቱ የማይሰማቸውና ለነፍሳት ግድ የማይላቸው ተጠያቂነታቸው ትልቅ ነው፡፡ እውነት እንዳላቸው የሚናገሩ ወንዶችና ሴቶች ይነሱ፣ የክርስቶስን ቀንበር ይሸከሙ፣ የእርሱን ሸክም ይሸከሙ፡፡ የሚፈለጉ ሰዎች የይስሙላ ፍላጎት ያላቸው ሳይሆኑ ራስ ወዳድነት የሌለውና ክርስቶስን የሚመስል ፍላጎት ያላቸው ናቸው፤ ችግር ሲገጥመው የሚደክም ወይም ጥያቄ ሲበዛበት የሚቀዘቅዝ ፍላጎት ሳይሆን ጥልቅ ግለት ያላቸው ናቸው፡፡Amh2SM 381.5

    በአሜሪካ አገር በእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላለው ሕዝብ ጆሮ መናገር እፈልጋለሁ፡፡ ከሙታን ተነሱ፣ ክርስቶስ ሕይወት ይሰጣችኋል፡፡ በክርስቶስ ያለውን የእውነት ብርሃን ከማጣት የተነሳ ነፍሳት እየጠፉ ናቸው፡፡ በዘላለማዊው ዓለም ወሰን ላይ ቁመናል፡፡ ለዚህ ሥራ የጥሩ ጊዜ ክርስቲያኖች አይፈለጉም፡፡ ለዚህ ጊዜ ስሜትን የሚነካና ጣፋጭ ኃይማኖት አይፈለግም፡፡ በእምነታችንና እውነትን በማወጅ ሥራ ውስጥ ጥልቅ የሆነ ግለት መኖር አለበት፡፡ ከዚህ በፊት ተገንዝበን ከምናውቀው በበለጠ አዲስ ኃይል ለመሥራት ከሰይጣናዊ ወኪሎች አዲስ ሕይወት እየወጣ መሆኑን እነግራችኋለሁ፡፡ ከላይ የሆነ አዲስ ኃይል የእግዚአብሔርን ሕዝብ መቆጣጠር የለበትምን? እውነት በሚቀድሰው ተጽዕኖው ለሕዝብ መቅረብ አለበት፡፡ እንደ ሕዝብ ተስፋዎቻችን በሰዎች ግምት ላይ ሳይሆን በዘላለማዊ እውነታዎች ላይ እንዲመሰረት ልባዊ የሆኑ ተማጽእኖዎች፣ የመቃተት ጸሎቶች ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለባቸው፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ባለው ማስረጃ በመመስረት በእምነት እንዳለንና ወደ ሰማይ እየሄድን እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ለራሳችን ማወቅ አለብን፡፡Amh2SM 382.1

    ባሕርይን በተመለከተ የግብረገብ መስፈርት የእግዚአብሔር ሕግ ነው፡፡ መስፈርቶቹን እናሟላለንን? የእግዚአብሔር ሕዝብ ንብረታቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ መክሊቶቻቸውን እና ተጽእኖዎቻቸውን በሙሉ ወደ ወቅቱ ሥራ እያመጡ ናቸውን? እንነሳ፡፡ «ከክርስቶስ ጋር ከተነሳችሁ ክርስቶስ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ባለበት ያሉትን ነገሮች እሹ» (ቆላ. 3፡ 1)፡፡ Letter 55, 1886.Amh2SM 382.2

    ወደ ዘመን ፍጻሜ ስንቃረብ ሕብረቶች እየበዙ ይሄዳሉ፡፡ እነዚህ ሕብረቶች የራሳቸውን አሳሳች መላምቶችን በሥራ ላይ የሚያውሉ አማኝ ነን ባዮች አዳዲስ ፓርቲዎችን በመመስረት እውነትን የሚቃወሙ ተጽእኖዎችን ይፈጥራሉ፡፡ ክህደት ይጨምራል፡፡ «አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያዳመጡ ኃይማኖትን ይክዳሉ» (1ጢሞ. 4፡1)፡፡ ወንዶችና ሴቶች የሰማይን ጌታ እግዚአብሔርን ለመቃወም ሕብረት ፈጥረው ሳለ ቤተ ክርሰቲያን ለጉዳዩ ነቅታ ያለችው በከፊል ነው፡፡ እግዚአብሔርን እናምናለን በሚሉ ሰዎች መካከል እጅግ ብዙ ጸሎት፣ እጅግ ብዙ ልባዊ ጥረት ያስፈልጋል፡፡Amh2SM 383.1

    የእግዚአብሔርን መንግሥት የመገንባት ሥራን ለመቃወም በሚደረገው በዚህ የመጨረሻው ታላቁ ተጋድሎ ውስጥ የሰይጣን ወኪሎች በሰብዓዊ መልክ ይሳተፋሉ፡፡ የሰማይ መላእክትም ሰብአዊ መልክ በመውሰድ ተጋድሎው በሚደረግበት መስክ ይገኛሉ፡፡ የዚህ ዓለም ታሪክ የመጨረሻው ታላቅ ምዕራፍ እስከሚዘጋበት ጊዜ ድረስ እነዚህ ሁለቱ ተቃራኒ አካሎች መኖራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ የሰይጣን ወኪሎች በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ናቸው፡፡ ለአንድአፍታም እንኳን ቢሆን ከመጠበቂያችን ውጭ መሆን አንችልም፡፡ እውነተኛ የሆኑና ራሳቸውን የሚገዙ አማኞች ብዙ ይጸልያሉ፣ የሚከተለው ውጤት አነስተኛ ስለሆኑ ነገሮች ትንሽ ይናገራሉ፡፡ ደካሞችንና ችግረኞችን ለማደፋፈር ጠንካራ የሆኑ ምስክርነቶች ከከናፍሮቻቸው ይወጣሉ፡፡ አሁን ያለንበት ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብ ደካሞች፣ ወይም አንዱን ወይም ሌላ ነገር የሚሆኑበት ጊዜ አይደለም፡፡ ሁሉም ትጉህ የቃሉ ተማሪዎች ይሁኑ፡፡ በጌታ እና በኃይሉ ብርታት የበረታን መሆን አለብን፡፡ የዘፈቀደ ሕይወት እየኖርን እውነተኛ ክርስቲያኖች መሆን አንችልም፡፡ The Review and Herald, Aug. 5, 1909.Amh2SM 383.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents