Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከዓለም ጋር ሕብረት አለመፍጠር

    የእግዚአብሔርን ሕግ ከሚጥሱት ጋር ምንም ዓይነት ድርድር መኖር የለበትም፡፡ በእነርሱ ላይ እንደ መካሪዎች መታመን አደጋ አለው፡፡ የአሁኑ ምስክርነታችን ከቀድሞው ያነሰ ጥንካሬ ሊኖረው አይገባም፤ ትክክለኛው አቋማችን የዓለምን ታላላቅ ሰዎች ለማስደሰት ሲባል መሸፈን የለበትም፡፡ ከእነርሱ ጋር እንድንተባበርና እቅዳቸውን እንድንቀበል ሊፈልጉ ይችላሉ፣ መከተል የሚገባንን የተግባር አቅጣጫ በተመለከተም ለጠላት መልካም አጋጣሚ ሊሰጡ የሚችሉ ሀሳቦችን ሊያዘጋጁ ይችላሉ፡፡ «ይህ ሕዝብ ሕብረት በሚሉት ሁሉ ሕብረት ነው አትበሉ» (ኢሳ. 8፡12)፡፡ ተቃርኖን መፈለግ ባይኖርብንም፣ አስፈላጊ ባልሆነ ጉዳይ ላይ ጥፋት መፈጸም ባይኖርብንም፣ እውነትን በግልጽና በቁርጠኝነት ማቅረብና እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ባስተማረን ነገር ጸንተን መቆም አለብን፡፡ ምን መጻፍ ወይም ማሳተም ወይም መናገር እንዳለባችሁ ለመማር ከዓለም መጠበቅ የለባችሁም፡፡ ንግግራችሁና ተግባራችሁ «በብልጠት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል” (2 ጴጥ. 1፡16) የተባለውን ይመስክር፡፡ «ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፣ ምድር እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብረት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየተጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ” (2 ጴጥ. 1፡19)፡፡Amh2SM 371.1

    ሐዋሪያው ጳውሎስ እንዲህ በማለት ይነግረናል፣ «በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኗልና» (1 ቆሮ. 1፡21)፡፡ ይህ የራሳቸውን ኃይል ለማጉላት ሁል ጊዜ የሚፈተኑ ሰዎችን ለማሳመንና ለመለወጥ የእግዚአብሔርን አላማ መፈጸም ነበር፡፡ ሰዎች በራሳቸው ውስን ጥበብ የእውነትን እውቀት ማግኘት እንደሚችሉ ወይም እንደማይችሉ፣ ፈጣሪ አምላካቸውን ማወቅ እንደሚችሉ ወይም እንደማይችሉ፣ ጌታ ይገልጣል፡፡ ክርስቶስ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ ሙከራው ሙሉ በሙሉ ተደርጎ ሰዎች የሚኩራሩበት ጥበብ ሞኝነት እንደሆነ ተረጋገጠ፡፡ እግዚአብሔርን በተመለከተ ውስን ጥበብ ከትክክለኛው ድምዳሜ ላይ ለመድረስ በፍጹም አልቻለም ነበር፤ ስለዚህ ሰው የእግዚአብሔርን ሕግ በተመለከተ ፍርድ ለመስጠት በፍጹም ብቃት አልነበረውም፡፡ ከፍ ከፍ ባለው ስህተት ልክ እውነት ከዚያ ወደሚበልጥ ከፍታ እንዲነሳ በኃይል ለመሥራት እንዲቻል ስህተት ከእውነት በላይ ከፍ በማለት በዘመናችን ችግር እንዲከሰት ጌታ ሁኔታዎችን ፈቅዷል፡፡ Amh2SM 371.2

    ጌታ ዓይኖቹን በሕዝቡ ላይ በማድረግ በድካማቸው የእርሱን እርዳታ ብቻ እንዲጠባበቁ ለማድረግ በተደጋጋሚ ሁኔታዎች ወደ አስጨናቂ ደረጃ እንዲደርሱ ፈቅዷል፡፡ ጸሎታቸውና እምነታቸው እውነተኛ ለመሆን ካለቸው ጽኑ ዓላማ ጋር የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት እንደሚያስፈልግ ያሳየ ሲሆን እርሱም «የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮሃለህ እርሱም እነሆኝ ይላል (ኢሳ. 58፡9) የተባለውን ተስፋውን ፈጽሟል፡፡ ብርቱ የሆነው እጁ ሕዝቡን ነጻ ለማውጣት ተዘርግቷል፡፡ እነርሱ ደካማነታቸውን እስኪረዱ ድረስ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የሚያደርጋውን በጸጋ የተሞላ ጣልቃ ገብነት አይፈጽምም፡፡ በመሆኑም ነጻ መውጣታቸውን እጅግ የጎላና ድላቸውን ባለ ግርማ ያደርጋል፡፡ የሰው ጥበብ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ሲሆን የእግዚአብሔር ጣልቃ መግባት የበለጠውን ግልጽ ሆኖ ይታያል፣ ለእርሱ የሚገባውን ክብርም ይቀበላል፡፡ የእምነታችን ጠላቶች፣ አሳዳጆቻችን እንኳን፣ እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመመለስ ለእነርሱ እየሰራ እንደሆነ ይመለከታሉ፡፡Amh2SM 372.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents