Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 47—ለመጨረሻው አስጨናቂ ጊዜ መዘጋጀት

    ወንድሞችና እህቶች ሆይ! የሰባተኛ ቀን አክባሪ አድቬንቲስቶች እንደመሆናቸሁ ይህ ስም የሚወክለውን ሁሉ ሆናችሁ እንድትገኙ እማጸናችኋለሁ፡፡ ከመልእክቱ መንፈስ የመለየት አደጋ አለ፡፡Amh2SM 367.1

    የእግዚአብሔር ህዝብ በዓለም አስተሳሰቦችና ልምምዶች መመራት የለበትም፡፡ አዳኙ ለደቀመዛሙርቱ ያለውን አድምጡ፣ «እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፡፡ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ» (ዮሐ 14፤16*17)፡፡ «የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፣ እንዲሁም ነን» (1ኛ ዮሐ 3፤1)፡፡ Amh2SM 367.2

    ዓለም የእግዚአብሔርን ሕግ እንደምትረግጥ ሕጉም እንደሚቀለድበት ቃሉ በግልፅ ይናገራል፡፡ ኃጢአት ከተለመደው ወጣ ባለ ሁኔታ ይታያል፡፡ የፕሮቴስታንት አለም ከኃጢአት ሰው ጋር ሕብረት ይፈጥርና ቤተክርስቲያን እና ዓለም የተበላሸ ስምምነት ይኖራቸዋል፡፡Amh2SM 367.3

    በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግር እየመጣ ነው፡፡ ጳጳሳዊው ኃይል ከዚህ በፊት ያጣውን የበላይነት መልሶ እንደሚያገኝና ጊዜውን ለመምሰል ሲል ስምምነት በሚፈጥረውና የፕሮቴስታንት ዓለም ተብሎ በሚጠራው ኃይል አማካይነት እንደ እሳት ያለ ስደት እንደሚቀጣጠል የእግዚአብሔር ቃል ያስተምራል፡፡ በዚህ አስጨናቂ ጊዜ መቆም የምንችለው እውነትና የእግዚአብሔር ኃይል ሲኖረን ብቻ ነው፡፡ ሰዎች እውነትን ማወቅ የሚችሉት ራሳቸው የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡ አሁን ቅዱሳን መጻሕፍትን ስናነብና ስንመረምር ሳለ ከሰብዓዊ ጥበብ በላይ የሆነ ነገር ያስፈልገናል፤ ወደ እግዚአብሔር ቃል ትሁት በሆነ ልብ ብንቀርብ እርሱ እኛን ለመከላከል ሕገ-ወጥ በሆኑ ኃይሎች ላይ አርማውን ያነሳል፡፡Amh2SM 367.4

    የመጀመሪያውን መታመናችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን መያዝ ከባድ ነው፡፡ ሌላ መንፈስን ለማምጣት የሚፈልጉ፤ ተቃራኒ የሆነ ሥራ የሚሰሩና በጉዳዩ በሰይጣን ወገን የሆኑ ኃይሎች ድብቅ ተጽእኖዎች ያለመታከት ሥራ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ አስቸጋሪነቱ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ስደት ካለመኖሩ የተነሳ አንዳንድ ትክክለኛ የሚመስሉና ክርስቲያን መሆናቸውም ምንም ጥያቄ የሌለባቸው፤ ነገር ግን ስደት ቢነሳ ከውስጣችን ወጥተው የሚሄዱ አንዳንድ ሰዎች እኛን ተቀላቅለዋል፡፡ በችግር ጊዜ በአእምሮዎቻቸው ውስጥ ተጽእኖ ያሳድር የነበረውን የማይረባ ኃይል ይመለከታሉ፡፡ የተለያዩ ዓይነት አእምሮዎችን ለመገናኘት ሰይጣን የተለያዩ አይነት ወጥመዶችን አዘጋጅቷል፡፡ የእግዚአብሔር ህግ ተቀባይነት በሚያጣበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ፈተናዎች ትበጠራለች፤ አሁን ከምንገምተው በላይ አብዛኛው ክፍል ለአሳሳች መናፍስትና ለሰይጣን አስተምህሮዎች ጆሮውን ይሰጣል፡፡ አጣብቂኝ የሆኑ ቦታዎች ላይ ሲደርሱ ከመበረታታት ይልቅ ብዙዎቹ በእውነተኛው የወይን ግንድ ላይ የተጣበቁ ህያዋን ቅርንጫፎች አለመሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ምንም ፍሬ ስላላፈሩ አትክልተኛው ያስወግዳቸዋል፡፡Amh2SM 368.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents