Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 33—«በፊቴ ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ”

    እያንዳንዱ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ስንዴ ይበጠራል፣ በመበጠሩ ሂደት ውስጥ አእምሮን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ከፍተኛ ዋጋ የተሰጠው ደስታ ሁሉ መስዋዕት መደረግ አለበት፡፡ በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ መደርደሪያዎች እና ጠረጴዛዎች በጌጣጌጦችና በፎቶዎች ተሞልተዋል፡፡ በቤተሰብ እና በጓደኞቻቸው ፎቶግራፎች የተሞሉ አልበሞች የእንግዶችን ትኩረት በሚስቡበት ቦታ ተቀምጠዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ በእግዚአብሔር እና በሰማያዊ ጉዳዮች ላይ ማረፍ ያለበት ሀሳብ ተራ ወደ ሆኑ ነገሮች እንዲወርድ ተደርጓል፡፡ ይህ የጣዖት አምልኮ ዝሪያ አይደለምን? ለዚህ ተግባር የዋለው ገንዘብ ለሰብአዊ ዘር በረከት ለመሆን፣ በመሰቃየት ላይ ያሉትን ከስቃያቸው ለመገላገል፣ የተራቆቱትን ለማልበስ እና የተራቡትን ለመመገብ መዋል አይችልምን? የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ፊት ለማስቀጠል እና የእርሱን መንግሥት በምድር ላይ ለመገንባት ወደ ጌታ ግምጃ ቤት መግባት የለበትምን?Amh2SM 317.1

    ይህ ነገር ታላቅ ጠቀሜታ ያለው ስለሆነ ከጣዖት አምልኮ ኃጢአት እንድትድኑ የተሰጠ ነው፡፡ በእሥራኤል ቅዱስ የተነገረውን ቃል ብትታዘዙ በነፍሳችሁ ላይ በረከት ይመጣላችኋል፡፡ «ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ በፊቴ” (ዘጸ. 20፡ 3)፡፡ ብዙዎች ቤታቸውን ለሞሉ አላስፈላጊ ጌጣጌጦች ጊዜና ሀሳብን በመስጠት ለራሳቸው አስፈላጊ ያልሆነ ጭንቀትና ስጋት እየጨመሩ ናቸው፡፡ ይህ ጊዜያቸውንና ሀሳባቸውን የሰጡት ነገር በሁሉም መልኩና ተግባሩ ጣዖት አምልኮ ስለሆነ የሚቀሰቅሳቸው የእግዚአብሔር ኃይል ያስፈልጋል፡፡ Amh2SM 317.2

    ልብን የሚመረምር አምላክ ሕዝቡን ከእያንዳንዱ የጣዖት አምልኮ ሊያላቅቅ ይመኛል፡፡ አሁን በማይጠቅሙ ጌጣጌጦች የተሞሉ ጠረጴዛዎችን የእግዚአብሔር ቃል፣ የተባረከው የእግዚአብሔር ቃል ይያዝ፡፡ ገንዘባችሁን የወቅቱን እውነት በተመለከተ የአእምሮ ማስተዋልን የሚጨምሩ መጻሕፍትን ለመግዛት አውሉ፡፡ በቤታችሁ ውስጥ ያሉትን በርካታ ጌጣጌጦች ለማንቀሳቀስና አቧራቸውን ለማራገፍ የምታባክኑትን ጊዜ ለጓደኞቻችሁ ጥቂት መስመሮችን ለመጻፍ፣ እውነትን ለማያውቅ ለአንድ ሰው በራሪ ገጾችን ወይም ትንንሽ መጻሕፍትን ለመላክ አውሉት፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ዘላለማዊ ጥበብ እና ፍቅር ሀብት አድርጋችሁ ያዙት፤ ይህ የሰማይን መንገድ የሚያመለክት መሪ መጽሐፍ ነው፡፡ «እነሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ” (ዮሐ. 1፡ 29) በማለት ኃጢአትን ይቅር ወደሚለው አዳኝ ያመላክት፡፡Amh2SM 318.1

    በጸሎት በተሞላ ልብና ለእግዚአብሔር በመገዛት መንፈስ ቅዱሳን መጻሕፍትን ምነው በመረመራችሁ! ሻማ በርቶ ዕቃ እንደሚፈለግ ምነው ልባችሁን በመረመራችሁ እና አእምሮን ከእግዚአብሔር መንገድ ከሚያርቁ ዓለማዊ ልማዶች ጋር የሚያቆራኘውን ስስ ክር አግኝታችሁ በቆረጣችሁት! ሀሳባችሁንና ፍቅራችሁን ከእርሱ የሚወስደውን እያንዳንዱን ልምምድ እንዲያሳያችሁ እግዚአብሔርን ለምኑት፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ቅዱስ ሕጉን የሰጠው እንደ ባሕርይ መለኪያ አድርጎ ነው፡፡ በዚህ ሕግ አማካይነት በባሕርይህ ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ጉድለት ማየትና ማሸነፍ ትችላለህ፡፡ ራሳችሁን ከእያንዳንዱ ጣዖት በመለየት በጸጋና በእውነት ወርቃማ ሰንሰለት ከእግዚአብሔር ዙፋን ጋር ማገናኘት ትችላላችሁ፡፡ The Review and Herald, May 14, 1901.Amh2SM 318.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents