Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 7—መለኮታዊ መረጃዎች

    የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ባቢሎን ተብሎ ወደተገለጸው ወደ ዝቅተኛ ደረጃ ወድቃለች ወደሚለው ድምዳሜ ለደረሰ አንድ ሰው የጻፈችው ደብዳቤ እንደሚከተለው ይቀርባል፡- አሰባሳቢዎች ውድ ወንድም ኤም፣ የላክልኝ ደብዳቤ በሰንበት ጅምር ላይ ደርሶኝ ተቀብያለሁ፡፡.... ትምህርት ቤት እንድትገባና እንድትማር፣ እውነትን በተመለከተ አእምሮህ በደንብ እስኪረጋጋ ድረስ ይህን አገር ለቀህ እንዳትሄድ እመክርሃለሁ፡፡ የዚህን መንፈቅ ትምህርት እንደምትከታተልና ወደ ዓለም መወሰድ ስላለበት የእውነት መልእክት የምትችለውን ሁሉ እንደምትማር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡{2SM 63.1}Amh2SM 63.1

    የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያንን ባቢሎን ብለህ እንድትጠራና የእግዚአብሔር ሕዝብ ከእሷ እንዲወጣ ጥሪ እንድታቀርብ እግዚአብሔር መልእክት አልሰጠህም፡፡ ጌታ ይህን ከሚመስል መልእክት ተቃራኒ የሆነ ግልጽ ብርሃን ስለሰጠኝ አንተ የምታቀርባቸው ምክንያቶች ሁሉ በእኔ ዘንድ ክብደት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ {2SM 63.2}Amh2SM 63.2

    ቅንነትህንና ታማኝነትህን አልጠራጠርም፡፡ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ባቢሎን እንደሆነች ይከሱ ለነበሩ ሰዎች እውነትን እንዳልያዙ በመግለጽ በተለያዩ ጊዜያቶች ረጃጅም ደብዳቤዎችን ጽፌላቸዋለሁ፡፡ ሰዎች አእምሮዬ ሚዛናዊ እንዳይሆን አድርገዋል ብለህ ታስባለህ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ከሆንኩ የእግዚአብሔር ሥራ አደራ ሊሰጠኝ የተገባሁ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ግለሰቦች ለሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን መልእክት አለን ብለው በተነሱበት በሌሎች ሁኔታዎችም ይህ ጉዳይ ወደ አእምሮ እንዲመጣ ተደርጓል፡፡ ለእኔም «አትመኑአቸው፣ እኔ አልላኳቸውም፣ ነገር ግን ይሮጣሉ» የሚል ቃል ተሰጥቶኛል፡፡ {2SM 63.3}Amh2SM 63.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents