Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የቀድሞው ታሪክ ሊደገም ነው

    አስቸጋሪ ወደ ሆነው ታሪክ ውስጥ አልገባም፤ እጅግ በጣም ብዙ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ስብሰባዎቻችን የስህተት ንድፈ ሀሳቦችና ዘዴዎች እንደሚመጡና ያለፈው ታሪክ እንደሚደገም እግዚአብሔር ባለፈው ጥር ወር አሳይቶኛል፡፡ እጅግ ተጨንቄ ነበር፡፡ በእነዚህ የስሜት መግለጫዎች አጋንንት በሰው መልክ ሆነው በመገኘት አስተዋይ የሆኑ ሰዎች እውነትን እንዲጠሉ ለማድረግ ሰይጣን ባለው ብልጠት ሁሉ እየሰራ እንደሆነ፤ የሶስተኛውን መልአክ መልእክት እውነት በሕዝብ ፊት የማቅረቢያ መንገድ መሆን ይችሉ የነበሩ ስብሰባዎች ኃይላቸውንና ተጽዕኖአቸውን እንዲያጡ ለማድረግ ሰይጣን ነገሮችን ለማዘጋጀት እየሞከረ መሆኑን እንድናገር ተነግሮኛል፡፡{2SM 37.3}Amh2SM 37.3

    የሶስተኛው መልአክ መልዕክት ቀጥ ባሉ መስመሮች ሊሰጥ ነው፡፡ የመጀመሪያ ወላጆቻችንን ለማታለል ሰይጣን ውብ የነበረውን እባብ እንደተጠቀመበት ሁሉ በውሸት አባት ተዘጋጅተው ከተደበቁ ከእያንዳንዱ ርካሽ እና አሳዘኝ የሰዎች የፈጠራ ንድፈ ሀሳቦች ነጻ ሆኖ ሊጠበቅ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በንጽህናው እንዲቆም በሚፈልገው ሥራ ላይ ሰይጣን የራሱን ማህተም ለማሳረፍ ይሞክራል፡፡ {2SM 37.4}Amh2SM 37.4

    ባለፈው ጥር ወር በፊቴ እንደታየው ባለ ምስቅልቅሉ በወጣ ጫጫታና ብዙ ድምጾች ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንም ድርሻ የለውም፡፡ ሰይጣን እንደዚህ ባለ የሙዚቃ ጋጋታ እና ምስቅልቅል መካከል ሥራውን ይሰራል፣ የዚህ ውጤት እንደ እባብ መርዝ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ሙዚቃ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ቢውል ኖሮ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ሊሆን ይችል ነበር፡፡ {2SM 37.5}Amh2SM 37.5

    ከዚህ በፊት የነበሩ ነገሮች ወደ ፊትም ይኖራሉ፡፡ ሰዎች በሚጠቀሙበት መንገድ ሰይጣን ሙዚቃን ወጥመድ ያደርገዋል፡፡ በቃሉና በምስክሮች ውስጥ በፊታቸው ብርሃን የተቀመጠላቸውን ሕዝቡን እንዲያነቡና እንዲያመዛዝኑ፣ እንዲሁም ልብ እንዲሉ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብላቸዋል፡፡ ሁሉም ማስተዋል እንዲችሉ ግልጽና እርግጠኛ የሆነ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡ ነገር ግን የሆነ አዲስ ነገር ለመፍጠር ያለው እረፍት የሚነሳ ፍላጎት እንግዳ የሆኑ አስተምህሮዎችን በማምጣት እግዚአብሔር በሰጣቸው እውነት ላይ የነበራቸውን የመጀመሪያውን መታመናቸውን አጥብቀው ቢይዙ ኖሮ ለመልካም ነገር ኃይል መሆን ይችሉ የነበሩትን ሰዎች ተጽእኖ ያበላሻል፡፡ {2SM 38.1}Amh2SM 38.1

    «ስለዚህ በማንኛውም ሰዓት ከእጃችን እንዳይሾልኩብን ለሰማናቸው ነገሮች የበለጠ ልባዊ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ በመላእክት የተነገረው ቃል የጸና ከሆነ፣ እያንዳንዱ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፣ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፣ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፣ የሰሙትም ለእኛ አጸኑት» (ዕብ. 2፡ 1-3)፡፡ «ወንድሞች ሆይ፣ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻ አጽንተን ብንጠብቅ፣ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና” (ዕብ 3፡ 12-14)፡፡ {2SM 38.2}Amh2SM 38.2

    ወንድም እና እህት ሃስከል፣ እያንዳንዱን የጦር ዕቃ መልበስ አለብን፣ ሁሉንም ካደረግን በኋላ ጸንተን መቆም አለብን፡፡ እንደ ወንጌል መከላከያ ስለተቀመጥን ኃይለኛ የሆነ ጦርነትን ለመዋጋት የጌታ ታላቅ ሰራዊት አካል መሆን አለብን፡፡ በጌታ ታማኝ አምባሳደሮች እውነት ግልጽ በሆነ ሁኔታ መቅረብ አለበት፡፡ ዛሬ የሚፈትን እውነት ተብሎ የሚጠራው አብዛኛው ነገር መንፈስ ቅዱስን ወደ መቋቋም የሚመራ ልፍለፋ ነው፡፡... {2SM 38.3}Amh2SM 38.3