Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወግ አጥባቂነት በመካከላችን ሊገለጽ ነው

    ወግ አጥባቂነት በመካከላችን ይታያል፡፡ ቢቻላቸው ኖሮ የተመረጡትን እንኳን ወደ ስህተት የመምራት ባሕርይ ያላቸው ማታለያዎች ይመጣሉ፡፡ በእነዚህ መገለጦች ውስጥ ተለይተው የሚታወቁ ስርአትን ያለመከተል ሁኔታዎችና እውነተኛ ያልሆኑ ንግግሮች ትክክል መስለው ከቀረቡ ከታላቁ መምህር ከንፈር የሚወጡ ቃላት አይፈለጉም፡፡ ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት ምክንያት ወደፊት ሊነሱ ያሉ ብዙ እና የተለያዩ ዓይነት አደጋዎች ስላሉ ነው፡፡ {2SM 16.4}Amh2SM 16.4

    የአደጋ ምልክትን ከፍ አድርጌ የምሰቅልበት ምክንያት በእግዚአብሔር መንፈስ መገለጥ ወንድሞቼ የማይረዱትን ነገር ማየት ስለምችል ነው፡፡ ራሳቸውን መጠበቅ ያለባቸውን ልዩ የሆኑ የማታለያ ምዕራፎችን ሁሉ መጠቆም አዎንታዊ የሆነ አስፈላጊ ነገር ላይሆን ይችላል፡፡ ራሳችሁን ጠብቁ ብዬ መንገር በቂዬ ነው፤ ሰዎች ከእግዚአብሔር እንደተነገራቸው የሚናገሩትን ነገር ሁሉ ሳይለዩ እንዳይቀበሉ የእግዚአብሔርን መንጋ እንደ ታማኝ ዘቦች ጠብቋቸው፡፡ ግርግር (ሽብር) ለመፍጠር ከሰራን፣ የፈለግነውን ሁሉ እና ከዚያም አልፎ መቆጣጠር ከምንችለው በላይ የሆነ ግርግር መፍጠር እንችላለን፡፡ በእርጋታና በግልጽ «ቃሉን ስበክ፡፡” ግርግር መፍጠርን ሥራችን እንደሆነ አድርገን መቁጠር የለብንም፡፡ {2SM 16.5}Amh2SM 16.5

    ጤናማ የሆነ ግለትን መፍጠር የሚችል የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይስራ፣ ሰብዓዊ ወኪል በመመልከት፣ በመጠበቅ፣ በመጸለይ፣ በእያንዳንዱ ሰዓት ወደ ኢየሱስ በመመልከት፣ ብርሃንና ሕይወት በሆነው ክቡር መንፈስ ቁጥጥር ስር በመሆን እርሱ ፊት በቀስታ ይሂድ፡፡ --Letter 68, 1894. {2SM 16.6}Amh2SM 16.6

    መጨረሻው ቅርብ ነው፡፡ የብርሃን ልጆች በፊታችን ላለው ታላቅ ክስተት እንዲዘጋጁ ሌሎችን ለመምራት እና መንፈስ ቅዱስ በልባቸው እንዲሰራ ስለፈቀዱ ጠላትን መቋቋም እንዲችሉ ለማድረግ ልባዊ በሆነና በማይሰለች ከፍተኛ ፍላጎት ሊሰሩ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወደ ስህተት ግርግር፣ ኃይማኖታዊ መነቃቃቶች እና ለማወቅ ወደ መጓጓት ለውጦች ለመምራት አዳዲስና እንግዳ የሆኑ ነገሮች በቀጣይነት ይነሳሉ፡፡ ዓይኖቻቸውን የዓለም ብርሃንና ሕይወት በሆነው ላይ በማተኮር ወደፊት መጓዛቸውን ይቀጥሉ፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ብርሃንና እውነት ተብሎ የተጠራው እያንዳንዱ ነገር፣ ከሰይጣን የብልጠት ዘዴ የተቀዳ ሳይሆን ከመለኮታዊ ጥበብ የሚመጣ ነገር እንደሆነ እወቁ፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ ብርሃን ለእያንዳንዱ እውነተኛ፣ ጽኑ እና ለኃጢአቱ ለሚጸጸት ነፍስ ለእግሩ እንደ መብራት ነው፡፡ --Letter 45, 1899. {2SM 17.1}Amh2SM 17.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents