Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የትልቅ ደሞዝ ጉዳት

    የክርስቶስ ሥጋ መልበስ ራስን መስዋዕት የማድረግ ተግባር ነው፤ ሕይወቱ ያለማቋረጥ ራስን የመካድ ሕይወት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ያለው ፍቅር ታላቅ ክብር የተገለጠው የአካሉ መገለጫ በሆነው በአንድያ ልጁ መስዋዕትነት ነበር፡፡ ይህ ትልቁ የአምልኮ ምስጢር ነው፡፡ የክርስቶስን አእምሮ ማግኘት የእያንዳንዱ የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ባይ ዕድልና ተግባር ነው፡፡ ራሳችንን ሳንክድና መስቀልን ሳንሸከም የእርሱ ደቀመዛሙርት መሆን አንችልም፡፡ Amh2SM 185.2

    በሪቪውና ሄራልድ ቢሮ ውስጥ ለሚሰሩት ከፍተኛ ደሞዝ እንዲከፈላቸው የውሳኔ ሀሳቦች ቀርበው ተቀባይነት ባገኙ ጊዜ ጠላት የእግዚአብሔርን ዓላማ ለመገልበጥ እና ነፍሳትን በስህተት መንገዶች ለመምራት በነበረው እቅድ እየተሳካለት ነበር፡፡ ራስ ወዳድነት የነበረበት የመስገብገብ መንፈስ ከፍተኛ ደሞዝን ተቀበለ፡፡ ሰራተኞቹ በክርስቶስ ትምህርቶች ውስጥ የተቀመጡ መርሆዎችን ተለማምደው ቢሆን ኖሮ እያወቁ እንደዚህ ያለውን ክፍያ አይቀበሉም ነበር፡፡ የዚህ ደሞዝ ጭማሪ ውጤት ምን ነበር? የቤተሰብ ኑሮ ወጪዎች በጣም ጨመሩ፡፡ በክርስቶስ ሕይወት ውስጥ ከተሰጡ መመሪያዎችና ምሳሌዎች መለየት ተከሰተ፡፡ ትዕቢት ተነቃቅቶ ተፈጻሚነት አገኘ፤ የተገኘው ገቢ በታይታና አስፈላጊ ባልሆነ የራስን ፍላጎት በማሟላት ላይ ዋለ፡፡ የዓለም ፍቅር ልብን ተቆጣጠረውና ቅድስና የሌለው ፍላጎት የነፍስን ቤተ መቅደስ ገዛው፡፡ ትልቅ ደሞዝ እርግማን ሆነ፡፡ ምሳሌው የዓለም እንጂ የክርስቶስ አልነበረም፡፡ Amh2SM 185.3

    የክርስቶስ ፍቅር የራስን ፍላጎት ወደመፈጸም አይመራም፣ ራስን ለማስደሰትና ከፍ ከፍ ለማድረግ ወይም በሰው ልብ ውስጥ ኩራትን ለማበረታታት ገንዘብን በማያስፈልግ ነገር ላይ ወጪ ወደማድረግ አይመራም፡፡ በልብ ውስጥ ያለ የኢየሱስ ፍቅር ሁልጊዜ ነፍስን ወደ ትህትናና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሙሉ በሙሉ ወደ መስማማት ይመራል፡፡--Letter 21, 1894.Amh2SM 186.1

    ኃጢአት ከውስጥ ሆኖ ጥቃት ሲያደርስ፣ የሚያጠቃው የሰውን ተፈጥሮ እጅግ የከበረውን ክፍል ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሚመስሉ የሰው ክፍሎችና ኃይሎች ላይ አሰቃቂ የሆነ ውዝግብና ሽብር ይፈጥራል፡፡ አካላዊ በሽታ አካልን እንዲሸነፍ ሲያደርግ የራስ ወዳድነትና የምኞት በሽታ ደግሞ ነፍስን ያፈነዳል፡፡--Letter 26, 1897.Amh2SM 186.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents