Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የፈተናዎች አገልግሎት

    [Appeared In Notebook Leaflets, Christian Experience, No. 7.]

    በክርስቲያን ልምምድ ውስጥ ወንዶችንና ሴቶችን ከፍ ወዳለ የኑሮ ደረጃ እና የበለጠውን ወደተቀደሰ አገልግሎት ለመጥራት ጌታ የተለያዩ ዓይነት ፈተናዎችን ይፈቅዳል፡፡ ያለ እነዚህ ፈተናዎች በቀጣይነት ክርስቶስን ከመምሰል ወደ ኋላ ማፈግፈግ ይኖራል፣ ሰዎች ከሰይጣን ተከታዮች ጋር አንድነት እንዲፈጥሩ በሚመራ ሳይንሳዊ፣ ግምታዊና ሰብዓዊ ፍልስፍና መንፈስ ይሞላሉ፡፡ {2SM 160.3}Amh2SM 160.3

    በእግዚአብሔር እይታ የእያንዳንዱን መልካምና ታላቅ ሥራ ንጽህናውን ለመፈተንና በሀላፊነት ቦታዎች የቆሙ ሰዎችን የመርሆዎች ጥንካሬ ለመፈተን፣ ግላዊ ሰብዓዊ ባሕርይን በእግዚአብሔር ምሳሌ ለመቅረጽና እውነትነትን ለማረጋገጥ ፈተና እንዲመጣባቸው ይፈቅዳል፡፡ ይህ ከሁሉ የሚበልጥ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ትምህርት ነው፡፡ {2SM 161.1}Amh2SM 161.1

    የባህርይ ፍጽምና ላይ መድረስ የሚቻለው ከፍተኛ በሆኑ የፈተና ጊዜያቶች የእግዚአብሔር ቃል ለሚጠይቀው ለእያንዳንዱ መስፈርት በመታዘዝ የአእምሮ ክፍሎችን በማሰራት ነው፡፡ መታመንን በሚጠይቁ ቦታዎች የተቀመጡ ሰዎች የእግዚአብሔርን ክብር ለማስተዋወቅ በእርሱ እጅ መሳሪያዎች መሆን አለባቸው፣ ተግባሮቻቸውን ከፍተኛ በሆነ ታማኝነት በማከናወን የባሕርይ ፍጽምና ላይ መድረስ ይችላሉ፡፡ {2SM 161.2}Amh2SM 161.2

    ለትክክለኛ መርሆዎች እውነተኛ በሆኑ ሰዎች ሕይወት ቀጣይነት ያለው በእውቀት ማደግ ይኖራል፡፡ ሰብዓዊ ዘርን በመወከል እየሰራ ካለው የሰራተኞች አለቃ ጋር አብረው ሰራተኞች የመሆን እድል ያገኛሉ፣ የእግዚአብሔርን ዓላማዎች በመፈጸም ረገድም የከበረ ተግባር ይፈጽማሉ፡፡ በመሆኑም በቃልና በሕይወት ምሳሌነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሰራተኞች እንደመሆናቸው፣ ፈጣሪያቸውን ያከብራሉ፡፡-- Undated manuscript 150. {2SM 161.3}Amh2SM 161.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents